قَدْ كَانَ لَكُمْ ءَايَةٌ فِى فِئَتَيْنِ ٱلْتَقَتَا فِئَةٌ تُقَٰتِلُ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَأُخْرَىٰ كَافِرَةٌ يَرَوْنَهُم مِّثْلَيْهِمْ رَأْىَ ٱلْعَيْنِ وَٱللَّهُ يُؤَيِّدُ بِنَصْرِهِۦ مَن يَشَآءُ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَعِبْرَةً لِّأُو۟لِى ٱلْأَبْصَٰرِ
Amharic Translation - Africa Academy13. በእነዚያ (የበድር) ቀን በተጋጠሙት ሁለት ቡድኖች ለእናንተ ብዙ ተዓምራት አሉ:: አንደኛዋ ቡድን በአላህ መንገድ ትጋደላለች:: ሌላይቱ ቡድን ደግሞ ከሓዲ ናት። በዓይን አስተያየት እጥፋቸው ሆነው ያዩዋቸዋል (በቁጥር የነርሱ እጥፍ ሁነው በአይናቸው ተመለከቷቸው)። አላህ በእርዳታው የሚሻውን ሁሉ ያበረታልና። በዚህ ውስጥ ለማስተዋል ባለቤቶች ሁሉ በእርግጥ መገሰጫ አለበት::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(የበድር ቀን) በተጋጠሙት ሁለት ጭፍሮች ለናንተ በእርግጥ ተዓምር አልለ፡፡ አንደኛዋ ጭፍራ በአላህ መንገድ ትጋደላለች፡፡ ሌላይቱም ከሓዲ ናት፡፡ ከሓዲዎቹ (አማኞቹን) በዓይን አስተያየት እጥፋቸውን ኾነው ያዩዋቸዋል፡፡ አላህም በርዳታው የሚሻውን ሰው ያበረታል፡፡ በዚህ ውስጥ ለማስተዋል ባለቤቶች በእርግጥ መገሰጫ አለበት፡፡