إِذْ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَىٰٓ إِنِّى مُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ إِلَىَّ وَمُطَهِّرُكَ مِنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَجَاعِلُ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوكَ فَوْقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ ثُمَّ إِلَىَّ مَرْجِعُكُمْ فَأَحْكُمُ بَيْنَكُمْ فِيمَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡- «ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጅህና ከምድር ወደ እኔ አንሽህ ነኝ:: ከነዚያም በእኔ ከካዱ ሰዎች (ተንኮል) አጥሪህ ነኝ። እነዚያ የተከተሉህንም እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ:: ከዚያ የሁላችሁም መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው:: ያን ትለያዩበት በነበራችሁበት ነገርም በመካከላችሁ እፈርዳለሁ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህም ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጂህ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ፡፡ ከነዚያም ከካዱት ሰዎች አጥሪህ ነኝ እነዚያንም የተከተሉህን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደእኔ ነው፡፡ በርሱ ትለያዩበትም በነበራችሁት ነገር በመካከላችሁ እፈርዳለሁ፡፡