caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Aal-i-Imraan፣ አንቀጽ 81

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 89 · 3:81

وَإِذْ أَخَذَ ٱللَّهُ مِيثَٰقَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ لَمَآ ءَاتَيْتُكُم مِّن كِتَٰبٍ وَحِكْمَةٍ ثُمَّ جَآءَكُمْ رَسُولٌ مُّصَدِّقٌ لِّمَا مَعَكُمْ لَتُؤْمِنُنَّ بِهِۦ وَلَتَنصُرُنَّهُۥ قَالَ ءَأَقْرَرْتُمْ وَأَخَذْتُمْ عَلَىٰ ذَٰلِكُمْ إِصْرِى قَالُوٓا۟ أَقْرَرْنَا قَالَ فَٱشْهَدُوا۟ وَأَنَا۠ مَعَكُم مِّنَ ٱلشَّٰهِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy81. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «መጽሐፍንና ጥበብን ሰጥቻችሁ ከዚያ ከናንተ ጋር ላለው መጽሀፍ የሚያረጋግጥ መልዕክተኛ ቢመጣላችሁ በእርሱ እንድታምኑበት እንድትረዱትም።» ሲል አላህ የነቢያትን ቃል ኪዳን በያዘ ጊዜ (የነበረውን ክስተት ለህዝቦችህ አስታውስ)። «አረጋገጣችሁን? በዚህስ ላይ ቃል ኪዳኔን ያዛችሁን?» አላቸው። እነርሱም «አዎ አረጋገጥን» አሉ። «እንግዲያውስ መስክሩ:: እኔም ከናንተ ጋር ከመስካሪዎቹ ነኝ።» አላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ የነቢያትን ቃል ኪዳን ከመጽሐፍና ከጥበብ ሰጥቻችሁ ከዚያም «ከእናንተ ጋር ላለው (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥ መልክተኛ ቢመጣላችሁ በርሱ በእርግጥ እንደምታምኑበት በእርግጥም እንድትረዱት ሲል በያዘ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ አረጋገጣችሁን በዚህም ላይ ኪዳኔን ያዛችሁምን» አላቸው፡፡ «አረጋገጥን» አሉ፡፡ «እንግዲያስ መስክሩ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ከመስካሪዎቹ ነኝ» አላቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70