فَلَمَّا وَضَعَتْهَا قَالَتْ رَبِّ إِنِّى وَضَعْتُهَآ أُنثَىٰ وَٱللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا وَضَعَتْ وَلَيْسَ ٱلذَّكَرُ كَٱلْأُنثَىٰ وَإِنِّى سَمَّيْتُهَا مَرْيَمَ وَإِنِّىٓ أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ ٱلشَّيْطَٰنِ ٱلرَّجِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy36. በወለደቻትም ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! ሴት ሆና ወለድኳት።» አለች። አላህ የወለደችውን ምንነት አዋቂ ነው:: የተመኘችው ወንድ እንደ ወለደቻት ሴት የሚሆን አልነበረም:: «መርየምም ብዬ ስም አወጣሁላት:: እኔም እርሷንና ዝርያዋን ከተረገመው ሰይጣን ተንኮል ባንተ እጠብቃቸዋለሁ።» አለች።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበወለደቻትም ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! እኔ ሴት ኾና ወለድኋት፡፡» አላህም የወለደችውን ዐዋቂ ነው፡፡ «ወንድም እንደ ሴት አይደለም፡፡ እኔም መርየም ብዬ ስም አወጣሁላት፡፡ እኔም እስዋንም ዝርያዋንም ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ» አለች፡፡