caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Aal-i-Imraan፣ አንቀጽ 20

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 89 · 3:20

فَإِنْ حَآجُّوكَ فَقُلْ أَسْلَمْتُ وَجْهِىَ لِلَّهِ وَمَنِ ٱتَّبَعَنِ وَقُل لِّلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْأُمِّيِّـۧنَ ءَأَسْلَمْتُمْ فَإِنْ أَسْلَمُوا۟ فَقَدِ ٱهْتَدَوا۟ وَّإِن تَوَلَّوْا۟ فَإِنَّمَا عَلَيْكَ ٱلْبَلَٰغُ وَٱللَّهُ بَصِيرٌۢ بِٱلْعِبَادِ

Amharic Translation - Africa Academy20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢከራከሩህም «ፊቴን ለአላህ ብቻ ሰጠሁ። የተከተሉኝም እንደዚሁ ለአላህ ብቻ ሰጡ።» በላቸው:: ለእነዚያም መጽሐፉን ለተሰጡ ሰዎችና ለመሃይማኑ (ዐረቦች)፡- «ሰለማችሁን?» በላቸው:: ቢሰልሙም በእርግጥ ወደቀናው መንገድ ተመሩ:: እምቢ ቢሉ ግን ባንተ ላይ ያለብህ መልዕክትን ማድረስ ብቻ ነው:: አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqቢከራከሩህም፡- «ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ፤ የተከተሉኝም ሰዎች (እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ)» በላቸው፡፡ ለእነዚያም መጽሐፍን ለተሰጡት ሰዎችና ለመሐይሞቹ፡- «ሰለማችሁን» በላቸው፡፡ ቢሰልሙም በእርግጥ ተመሩ፡፡ እምቢ ቢሉም በአንተ ላይ ያለብህ ማድረስ ብቻ ነው፡፡ አላህም ባሮቹን ተመልካች ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70