فَنَادَتْهُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ وَهُوَ قَآئِمٌ يُصَلِّى فِى ٱلْمِحْرَابِ أَنَّ ٱللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحْيَىٰ مُصَدِّقًۢا بِكَلِمَةٍ مِّنَ ٱللَّهِ وَسَيِّدًا وَحَصُورًا وَنَبِيًّا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy39. እርሱም በዱዓ ማድረጊያ ክፍል ቆሞ ዱዓ ሲያደርግ መላዕክት:- «አላህ በየህያ: ከአላህ በሆነ ቃል የሚያረጋግጥ፣ በላጭ፣ ከሴት ጋር የማይገናኝ ድንግልና ከደጋጎቹም አንዱ ሲሆን ያበስርሃል።» በማለት መላዕክት ጠሩት።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእርሱም በጸሎት ማድረሻው ክፍል ቆሞ ሲሰግድ መላእክት ጠራችው፡፡ «አላህ በየሕያ ያበስርሃል፤ ከአላህ በኾነ ቃል የሚያረጋግጥ ጌታም ድንግልም ከደጋጎቹ ነቢይም ሲኾን » በማለት (መላእክት ጠራችው)፡፡