caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Aal-i-Imraan፣ አንቀጽ 140

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 89 · 3:140

إِن يَمْسَسْكُمْ قَرْحٌ فَقَدْ مَسَّ ٱلْقَوْمَ قَرْحٌ مِّثْلُهُۥ وَتِلْكَ ٱلْأَيَّامُ نُدَاوِلُهَا بَيْنَ ٱلنَّاسِ وَلِيَعْلَمَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَيَتَّخِذَ مِنكُمْ شُهَدَآءَ وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy140. አማኞች ሆይ! የመቁስል ጉዳት ቢያገኛችሁ ሌሎች ህዝቦችም መሰሉ የመቁሰል ጉዳት አግኝቷቸዋል። እንዲሁ ቀናትን በሰዎች መካከል እናፈራርቃቸዋለን:: አላህ እነዚያን በትክክል በሱ ያመኑትን ሊለይና ከእናንተም መካከል ሰማዕታትን ሊመርጥ እንዲህ አይነት ቀናት እንዲፈራረቁ ያደርጋል:: አላህም በዳዮችን ሁሉ አይወድምና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqቁስል ቢያገኛችሁ ሰዎቹንም መሰሉ ቁስል አግኝቷቸዋል፡፡ ይኽችንም ቀናት በሰዎች መካከል እናዘዋውራታለን፡፡ (እንድትገሰጹና) አላህ እነዚያን ያመኑትን እንዲያውቅ (እንዲለይ) ከእናንተም ሰማዕታትን እንዲይዝ ነው፡፡ አላህም በዳዮችን አይወድም፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70