يَوْمَ تَجِدُ كُلُّ نَفْسٍ مَّا عَمِلَتْ مِنْ خَيْرٍ مُّحْضَرًا وَمَا عَمِلَتْ مِن سُوٓءٍ تَوَدُّ لَوْ أَنَّ بَيْنَهَا وَبَيْنَهُۥٓ أَمَدًۢا بَعِيدًا وَيُحَذِّرُكُمُ ٱللَّهُ نَفْسَهُۥ وَٱللَّهُ رَءُوفٌۢ بِٱلْعِبَادِ
Amharic Translation - Africa Academy30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያን ነፍስ ሁሉ ከመልካም ነገር የሰራችውን የቀረበ ሆኖ የምታገኝበትን ቀን (አስታውስ):: ከመጥፎም የሰራችው በእርሷና በኃጢአቱ መካከል በጣም የሰፋ ርቀት ቢኖር ትመኛለች:: አላህ እራሱን ያስጠነቅቃችኋል:: አላህ ለባሮቹ ሩህሩህ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqነፍስ ሁሉ ከመልካም ነገር የሠራችውን የቀረበ ኾኖ የምታገኝበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ከመጥፎም የሠራችው በርስዋና በርሱ (በኀጢአትዋ) መካከል በጣም የሰፋ ርቀት ቢኖር ትመኛለች፡፡ አላህ ነፍሱን ያስጠነቅቃችኋል፡፡ አላህም ለባሮቹ ሩኅሩኅ ነው፡፡