قُلْ أَؤُنَبِّئُكُم بِخَيْرٍ مِّن ذَٰلِكُمْ لِلَّذِينَ ٱتَّقَوْا۟ عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّٰتٌ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَأَزْوَٰجٌ مُّطَهَّرَةٌ وَرِضْوَٰنٌ مِّنَ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ بَصِيرٌۢ بِٱلْعِبَادِ
Amharic Translation - Africa Academy15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከዚህ ከተዋበላችሁ ጉዳይ የሚበልጥን ልንገራችሁን? እርሱም ለእነዚያ አላህን ለሚፈሩ ሁሉ በጌታቸው ዘንድ በስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ሁልጊዜ ነዋሪዎች ሲሆኑ ንጹህ ሚስቶችና ከአላህ የሆነ ውዴታም አለላቸው:: አላህም ባርያዎቹን ተመልካች ነው።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ከዚህ ሁሉ ነገር የሚበልጥን ልንገራችሁን» በላቸው፡፡ (እርሱም) «ለእነዚያ ለተጠነቀቁት ሰዎች በጌታቸው ዘንድ በሥራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች (አላቸው) በውስጧ ሁልጊዜ ነዋሪዎች ሲኾኑ ንጹሕ የተደረጉ ሚስቶችም፣ ከአላህም የኾነ ውዴታ አላቸው፡፡ አላህም ባሮቹን ተመልካች ነው፡፡»