وَلِيَعْلَمَ ٱلَّذِينَ نَافَقُوا۟ وَقِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا۟ قَٰتِلُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ أَوِ ٱدْفَعُوا۟ قَالُوا۟ لَوْ نَعْلَمُ قِتَالًا لَّٱتَّبَعْنَٰكُمْ هُمْ لِلْكُفْرِ يَوْمَئِذٍ أَقْرَبُ مِنْهُمْ لِلْإِيمَٰنِ يَقُولُونَ بِأَفْوَٰهِهِم مَّا لَيْسَ فِى قُلُوبِهِمْ وَٱللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يَكْتُمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy167. እነዚያንም የነፈቁትንና «ኑ በአላህ መንገድ ተጋደሉ ወይም ተከላከሉ።» የተባሉትን ሊገልጽ ነው ይህን ያደረገው። አስመሳዮቹም «ውጊያን ብናውቅ ኖሮ በተከተልናችሁ ነበር።» አሉ:: እነርሱም ያን ጊዜ ከእምነት ይልቅ ወደ ክህደት የቀረቡ ናቸው:: በልቦቻቸው የሌለውን በአፎቻቸው ይናገራሉ። አላህም የሚደብቁትን ሁሉ አዋቂ ነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያንም የነፈቁትንና ለነርሱ «ኑ፤ በአላህ መንገድ ተጋደሉ፤ ወይም ተከላከሉ፤» የተባሉትን ሊገልጽ ነው፡፡ «መዋጋት (መኖሩን) ብናውቅ ኖሮ በተከተልናችሁ ነበር» አሉ፡፡ እነርሱ ያን ጊዜ ከእምነት ይልቅ ወደ ክህደት የቀረቡ ናቸው፡፡ በልቦቻቸው የሌለውን በአፎቻቸው ይናገራሉ፡፡ አላህም የሚደብቁትን ዐዋቂ ነው፡፡