مَّا كَانَ ٱللَّهُ لِيَذَرَ ٱلْمُؤْمِنِينَ عَلَىٰ مَآ أَنتُمْ عَلَيْهِ حَتَّىٰ يَمِيزَ ٱلْخَبِيثَ مِنَ ٱلطَّيِّبِ وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُطْلِعَكُمْ عَلَى ٱلْغَيْبِ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَجْتَبِى مِن رُّسُلِهِۦ مَن يَشَآءُ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ وَإِن تُؤْمِنُوا۟ وَتَتَّقُوا۟ فَلَكُمْ أَجْرٌ عَظِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy179. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) አላህ መጥፎውን ከመልካሙ እስከሚለይ ድረስ አማኞችን እናንተ ባላችሁበት ሁኔታ ላይ የሚተዋቸው አይደለም:: አላህም ሩቁን ነገር የሚያሳውቃችሁ አይደለም:: ግን አላህ ከመልዕክተኞቹ የሚሻውን ይመርጣል:: እናም በአላህና በመልዕክተኞቹም እመኑ:: ብታምኑና ብትጠነቀቁ ለእናንተ ታላቅ ምንዳ አለላችሁ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ መጥፎውን ከመልካሙ እስከሚለይ ድረስ ምእምናንን እናንተ በርሱ ላይ ባላችሁበት (ኹኔታ) ላይ የሚተው አይደለም፡፡ አላህም ሩቁን ነገር የሚያሳውቃችሁ አይደለም፡፡ ግን አላህ ከመልክተኞቹ የሚሻውን ይመርጣል፡፡ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ፡፡ ብታምኑና ብትጠነቀቁም ለናንተ ታላቅ ምንዳ አላችሁ፡፡