وَلَا يَحْسَبَنَّ ٱلَّذِينَ يَبْخَلُونَ بِمَآ ءَاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِن فَضْلِهِۦ هُوَ خَيْرًا لَّهُم بَلْ هُوَ شَرٌّ لَّهُمْ سَيُطَوَّقُونَ مَا بَخِلُوا۟ بِهِۦ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ وَلِلَّهِ مِيرَٰثُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy180. እነዚያ አላህ ከችሮታው ከሰጣቸው ገንዘብ የሚነፍጉ ሰዎች ንፉግነት ደግ ተግባር አይምሰላቸው:: ይልቁንም እርሱ ለእነርሱ መጥፎ ባህሪ ነው:: ያንን በእርሱ የነፈጉበት ገንዘብ በትንሳኤ ቀን (እባብ ሆኖ) በአንገታቸው ይጠለቃሉ:: የሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ ብቻ ነው:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያም አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ገንዘብ የሚነፍጉ እርሱ ለእነሱ ደግ አይምሰላቸው፡፡ ይልቁንም፤ እርሱ ለነሱ መጥፎ ነው፡፡ ያንን በርሱ የነፈጉበትን በትንሣኤ ቀን (እባብ ኾኖ) ይጠለቃሉ፡፡ የሰማያትና የምድርም ውርስ ለአላህ ብቻ ነው፡፡ አላህም በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡