إِنَّ ٱلَّذِينَ تَوَلَّوْا۟ مِنكُمْ يَوْمَ ٱلْتَقَى ٱلْجَمْعَانِ إِنَّمَا ٱسْتَزَلَّهُمُ ٱلشَّيْطَٰنُ بِبَعْضِ مَا كَسَبُوا۟ وَلَقَدْ عَفَا ٱللَّهُ عَنْهُمْ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy155.(የመልዕክተኛችን ባልደረቦች ሆይ!) እነዚያ ሁለቱ ቡድኖች በተገናኙ ቀን ከናንተ የሸሹትን ሰዎች በዚያ በሰሩት ከፊል ምክንያት ያሳሳታቸው ሰይጣን ነው:: አላህ ከእነርሱ በእርግጥ ይቅር ብሏል:: አላህ መሀሪና ለቅጣት የማይቸኩል ታጋሽ ነውና።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያ ሁለቱ ጭፍሮች በተገናኙ ቀን ከእናንተ የሸሹት ሰዎች በዚያ በሠሩት ከፊል ምክንያት ያሳሳታቸው ሰይጣን ነው፡፡ አላህ ከነሱ በእርግጥ ይቅር አለ፡፡ አላህ መሓሪ በቅጣት የማይቸኩል ነውና፡፡