caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Aal-i-Imraan፣ አንቀጽ 110

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 89 · 3:110

كُنتُمْ خَيْرَ أُمَّةٍ أُخْرِجَتْ لِلنَّاسِ تَأْمُرُونَ بِٱلْمَعْرُوفِ وَتَنْهَوْنَ عَنِ ٱلْمُنكَرِ وَتُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَلَوْ ءَامَنَ أَهْلُ ٱلْكِتَٰبِ لَكَانَ خَيْرًا لَّهُم مِّنْهُمُ ٱلْمُؤْمِنُونَ وَأَكْثَرُهُمُ ٱلْفَٰسِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy110. (ሙስሊሞች ሆይ!) ለሰው ልጆች ከተገለፁት ሕዝቦች ሁሉ በላጭ ሆናችሁ:: ይኸዉም በመልካም ነገር ታዛላችሁ:: ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ:: በአላህም አንድነት ታምናላችሁና ነው:: የመጽሐፉ ሰዎችም ልክ እንደናንተው ባመኑ ኑሮ ለእነርሱ የተሻለ በሆነ ነበር። ከእነርሱ መካከል ትክክለኛ አማኞችም አሉ:: አብዛሀኞቻቸው ግን አመጸኞች ናቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለሰዎች ከተገለጸች ሕዝብ ሁሉ በላጭ ኾናችሁ በጽድቅ ነገር ታዛላችሁ፤ ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ፤ በአላህም (አንድነት) ታምናላችሁ፡፡ የመጽሐፉም ሰዎች ባመኑ ኖሮ ለነርሱ የተሻለ በኾነ ነበር፡፡ ከነርሱ አማኞች አሉ፡፡ አብዛኞቻቸው ግን አመጸኞች ናቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70