caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Aal-i-Imraan፣ አንቀጽ 159

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 89 · 3:159

فَبِمَا رَحْمَةٍ مِّنَ ٱللَّهِ لِنتَ لَهُمْ وَلَوْ كُنتَ فَظًّا غَلِيظَ ٱلْقَلْبِ لَٱنفَضُّوا۟ مِنْ حَوْلِكَ فَٱعْفُ عَنْهُمْ وَٱسْتَغْفِرْ لَهُمْ وَشَاوِرْهُمْ فِى ٱلْأَمْرِ فَإِذَا عَزَمْتَ فَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلْمُتَوَكِّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy159. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ ችሮታ ለዘብክላቸው:: አመለ መጥፎና ልበ ደረቅ በሆንክ ኖሮ ከአጠገብህ በተበተኑ ነበር:: ከእነርሱም ጥፋት ይቅር በል:: ለእነርሱም ከአላህ ምህረትን ለምንላቸው:: በሁሉም ነገር ላይ አማክራቸው:: ከዚያ ቁርጥ ሀሳብ ባደረገክ ጊዜ በአላህ ላይ ብቻ ተመካ:: አላህ በእርሱ ላይ ብቻ ተመኪዎችን ይወዳልና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከአላህም በኾነች ችሮታ ለዘብክላቸው፡፡ ዐመለ መጥፎ ልበ ደረቅም በኾንክ ኖሮ ከዙሪያህ በተበተኑ ነበር፡፡ ከእነርሱም ይቅር በል፡፡ ለእነርሱም ምሕረትን ለምንላቸው፡፡ በነገሩም ሁሉ አማክራቸው፡፡ ቁርጥ ሐሳብም ባደረግህ ጊዜ በአላህ ላይ ተመካ፡፡ አላህ በርሱ ላይ ተመኪዎችን ይወዳልና፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70