بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱتَّقُوا۟ رَبَّكُمُ ٱلَّذِى خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَٰحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَآءً وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ٱلَّذِى تَسَآءَلُونَ بِهِۦ وَٱلْأَرْحَامَ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلَيْكُمْ رَقِيبًا
Amharic Translation - Africa Academy1. እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁን፤ ከእርሷም መቀናጆዋን (ሀዋን) የፈጠረውንና ከሁለቱም ብዙ ወንዶችንና ብዙ ሴቶችን የበተነውን ጌታችሁን (አላህን) ፍሩ:: ያንንም በእርሱ የምትጠያየቁበትን አላህን (ከሚያስቆጡ) ተግባራትና ዝምድናዎችን (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ:: አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአዳም) የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን (ሔዋንን) የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን (ጌታችሁን ፍሩ)፡፡ ያንንም በርሱ የምትጠያየቁበትን አላህንና ዝምድናዎችንም (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ፡፡ አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና፡፡