وَإِنْ خِفْتُمْ شِقَاقَ بَيْنِهِمَا فَٱبْعَثُوا۟ حَكَمًا مِّنْ أَهْلِهِۦ وَحَكَمًا مِّنْ أَهْلِهَآ إِن يُرِيدَآ إِصْلَٰحًا يُوَفِّقِ ٱللَّهُ بَيْنَهُمَآ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيمًا خَبِيرًا
Amharic Translation - Africa Academy35. በመካከላቸውም ጭቅጭቅ መኖሩን ብትፈሩ (ብታውቁ) ከቤተሰቡና ከቤተሰቦቿ የተውጣጡ የቤተ ዘመድ ጉባኤ አዋቅሩ:: ሁለቱም እርቅን ቢሹ አላህ በመካከላቸው ያስማማቸዋል:: አላህ ግልጽንም ሆነ ውስጥንም አዋቂ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(እናንተ ዋቢዎች) የመካከላቸውንም ጭቅጭቅ ብታውቁ ከቤተሰቦቹ ሽማግሌን ከቤተሰቦችዋም ሽማግሌን ላኩ፡፡ ማስታረቅን ቢሹ አላህ በመካከላቸው ያስማማል፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነውና፡፡