وَلَوْلَا فَضْلُ ٱللَّهِ عَلَيْكَ وَرَحْمَتُهُۥ لَهَمَّت طَّآئِفَةٌ مِّنْهُمْ أَن يُضِلُّوكَ وَمَا يُضِلُّونَ إِلَّآ أَنفُسَهُمْ وَمَا يَضُرُّونَكَ مِن شَىْءٍ وَأَنزَلَ ٱللَّهُ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ وَكَانَ فَضْلُ ٱللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًا
Amharic Translation - Africa Academy113. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባንተ ላይ ባልነበረ ኖሮ ከእነርሱ የሆነ ቡድኖች ሊያሳስቱህ ባሰቡ ነበር:: ነፍሶቻቸውን እንጂ ሌላ አያሳስቱም:: በምንም አይጎዱህም:: አላህ ባንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ:: የማታውቀውን ሁሉ አስተማረህ:: የአላህ ችሮታ ባንተ ላይ ታላቅ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየአላህም ችሮታና እዝነቱ ባንተ ላይ ባልነበረ ኖሮ ከእነሱ የኾኑ ጭፍሮች ሊያሳስቱህ ባሰቡ ነበር፡፡ ነፍሶቻቸውንም እንጅ ሌላን አያሳስቱም፡፡ በምንም አይጐዱህም፡፡ አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ፡፡ የማታውቀውንም ሁሉ አስተማረህ፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡