caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Nisaa፣ አንቀጽ 155

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 92 · 4:155

فَبِمَا نَقْضِهِم مِّيثَٰقَهُمْ وَكُفْرِهِم بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَقَتْلِهِمُ ٱلْأَنۢبِيَآءَ بِغَيْرِ حَقٍّ وَقَوْلِهِمْ قُلُوبُنَا غُلْفٌۢ بَلْ طَبَعَ ٱللَّهُ عَلَيْهَا بِكُفْرِهِمْ فَلَا يُؤْمِنُونَ إِلَّا قَلِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy155. ቃል ኪዳናቸውን በማፍረሳቸው፤ በአላህ አናቅጽ በመካዳቸው፤ ነብያትን ያለ አግባብ በመግደላቸውና «ልቦቻችን ሽፍን ናቸው።» በማለታቸውም ምክንያት ረገምናቸው:: በእውነቱ በክህደታቸው ምክንያት አላህ በእርሷ ላይ አተመ:: ስለዚህ ጥቂትን እንጂ አያምኑም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqቃል ኪዳናቸውንም በማፍረሳቸው፣ በአላህም አንቀጾች በመካዳቸው፣ ነቢያትንም ያለ አግባብ በመግደላቸውና «ልቦቻችን ሽፍኖች ናቸው» በማለታቸው ምክንያት (ረገምናቸው)፡፡ በእውነቱ በክህደታቸው ምክንያት አላህ በርሷ (በልቦቻቸወ) ላይ አተመ፡፡ ስለዚህ ጥቂትን እንጅ አያምኑም፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70