لَّن يَسْتَنكِفَ ٱلْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ وَلَا ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ ٱلْمُقَرَّبُونَ وَمَن يَسْتَنكِفْ عَنْ عِبَادَتِهِۦ وَيَسْتَكْبِرْ فَسَيَحْشُرُهُمْ إِلَيْهِ جَمِيعًا
Amharic Translation - Africa Academy172. አል መሲህ ለአላህ ባሪያ ከመሆን ፈጽሞ አይጸየፍም:: ቀራቢዎች የሆኑ መላዕክትም እንዲሁ ለአላህ ባሪያ ከመሆን ፈጽሞ አይጸየፉም:: ወደ አላህ እርሱን ከመገዛት የሚጸየፉና የሚኮሩ ሁሉ አላህ ሁሉንም ወደ እርሱ በእርግጥ ይሰበስባቸዋል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአልመሲሕ (ኢየሱስ) ለአላህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፡፡ ቀራቢዎች የኾኑት መላእክትም (አይጠየፉም)፡፡ እርሱን ከመገዛት የሚጠየፍና የሚኮራም ሰው (አላህ) ሁሉንም ወደ እርሱ በእርግጥ ይሰበስባቸዋል፡፡