يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُونُوا۟ قَوَّٰمِينَ بِٱلْقِسْطِ شُهَدَآءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰٓ أَنفُسِكُمْ أَوِ ٱلْوَٰلِدَيْنِ وَٱلْأَقْرَبِينَ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَٱللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا فَلَا تَتَّبِعُوا۟ ٱلْهَوَىٰٓ أَن تَعْدِلُوا۟ وَإِن تَلْوُۥٓا۟ أَوْ تُعْرِضُوا۟ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا
Amharic Translation - Africa Academy135. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በነፍሶቻችሁ ወይም በወላጆችና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢሆንም እንኳ በትክክል ለፍትህ ቋሚዎች ለአላህ መስካሪዎች ሁኑ:: ሀብታም ወይም ድሃ ቢሆንም አላህ ከእነርሱ ለእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው:: እንዳታዳሉም ዝንባሌን አትከተሉ:: ምስክርን ብታጣምሙ ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሰሩት ነገር ላይ ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! በትክክል (ፍትሕ) ቀዋሚዎች በነፈሶቻችሁ ወይም በወላጆችና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ (ከእናንተ) ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም (መመስከርን) ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡