أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ نَصِيبًا مِّنَ ٱلْكِتَٰبِ يُؤْمِنُونَ بِٱلْجِبْتِ وَٱلطَّٰغُوتِ وَيَقُولُونَ لِلَّذِينَ كَفَرُوا۟ هَٰٓؤُلَآءِ أَهْدَىٰ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ سَبِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ከመጽሐፉ ድርሻን ወደ ተሰጡት አላየህምን? በድግምትና በጣዖት ያምናሉ። ለእነዚያ በአላህ ለካዱትም እነርሱ በሃይማኖት ከእነዚያ በሙሐመድ ካመኑት ይበልጥ ቀና እንደሆኑ ይናገራሉ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወደ እነዚያ ከመጽሐፉ ዕድልን ወደ ተሰጡት አላየኸምን በድግምትና በጣዖት ያምናሉ፡፡ ለእነዚያም ለካዱት፡- እነዚያ (የካዱት) በመንገድ (በሃይማኖት) ከእነዚያ ካመኑት ይበልጥ የቀኑ ናቸው ይላሉ፡፡