إِنَّآ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ كَمَآ أَوْحَيْنَآ إِلَىٰ نُوحٍ وَٱلنَّبِيِّـۧنَ مِنۢ بَعْدِهِۦ وَأَوْحَيْنَآ إِلَىٰٓ إِبْرَٰهِيمَ وَإِسْمَٰعِيلَ وَإِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ وَٱلْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَٰرُونَ وَسُلَيْمَٰنَ وَءَاتَيْنَا دَاوُۥدَ زَبُورًا
Amharic Translation - Africa Academy163. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ወደ ኑህና ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነብያት መልዕክታችንን እንዳወረድን ሁሉ ወደ አንተም ቁርኣንን አወረድን:: ወደ ነብዩ ኢብራሂም፤ ወደ ነብዩ ኢስማኢልም፤ ወደ ነብዩ ኢስሃቅም፤ ወደ ነብዩ የዕቆብም፤ ወደ ነገዶችም፤ ወደ ነብዩ ዒሳም፤ ወደ ነብዩ አዩብም፤ ወደ ነብዩ ዩኑስም፤ ወደ ነብዩ ሃሩንና ወደ ነብዩ ሱለይማን አወረድን:: ለነብዩ ዳውድም ዘቡርን ሰጠነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩንና፣ ወደ ሱለይማንም አወረድን፡፡ ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው፡፡