يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِذَا ضَرَبْتُمْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ فَتَبَيَّنُوا۟ وَلَا تَقُولُوا۟ لِمَنْ أَلْقَىٰٓ إِلَيْكُمُ ٱلسَّلَٰمَ لَسْتَ مُؤْمِنًا تَبْتَغُونَ عَرَضَ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا فَعِندَ ٱللَّهِ مَغَانِمُ كَثِيرَةٌ كَذَٰلِكَ كُنتُم مِّن قَبْلُ فَمَنَّ ٱللَّهُ عَلَيْكُمْ فَتَبَيَّنُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا
Amharic Translation - Africa Academy94. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ መንገድ ለመዋጋት በተጓዛችሁ ጊዜ አረጋግጡ:: ሰላምታን ወደ እናንተ ላቀረበ ሰው የቅርቢቱን ሕይወት ጥቅም የምትፈልጉ ሆናችሁ «ትክክለኛ አማኝ አይደለህም።» አትበሉት:: አላህ ዘንድ ብዙ ምርኮዎች አሉና:: እናንተም ከዚህ በፊት ልክ እንደዚሁ ነበራችሁ:: አላህ በእናንተ ላይ ለገሰ:: ስለዚህም አረጋግጡ:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ መንገድ (ለመጋደል) በተጓዛችሁ ጊዜ አስረግጡ፡፡ ሰላምታንም ወደናንተ ላቀረበ ሰው የቅርቢቱን ሕይወት ጥቅም የምትፈልጉ ኾናችሁ ምእመን አይደለህም አትበሉ፡፡ አላህም ዘንድ ብዙ ዘረፋዎች አሉ፡፡ ከዚህ በፊት እንደዚሁ ነበራችሁ፡፡ አላህም በእናንተ ላይ ለገሰ ስለዚህ አስተውሉ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነውና፡፡