caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Nisaa፣ አንቀጽ 95

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 92 · 4:95

لَّا يَسْتَوِى ٱلْقَٰعِدُونَ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ غَيْرُ أُو۟لِى ٱلضَّرَرِ وَٱلْمُجَٰهِدُونَ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ بِأَمْوَٰلِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فَضَّلَ ٱللَّهُ ٱلْمُجَٰهِدِينَ بِأَمْوَٰلِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ عَلَى ٱلْقَٰعِدِينَ دَرَجَةً وَكُلًّا وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلْحُسْنَىٰ وَفَضَّلَ ٱللَّهُ ٱلْمُجَٰهِدِينَ عَلَى ٱلْقَٰعِدِينَ أَجْرًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy95. ከአማኞች የጉዳት ባለቤት ከሆኑት በስተቀር ተቀማጮቹ እና በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውም በነፍሶቻቸውም የሚታገሉት አይስተካከሉም:: በገንዘቦቻቸውም በነፍሶቻቸውም የሚታገሉትን አላህ በተቀማጮቹ ላይ በደረጃ አበለጠ:: ለሁሉም አላህ መልካሚቱን (ገነት) ተስፋ ሰጠ (ቃል ኪዳን ገባ):: ታጋዮቹንም በተቀማጮቹ ላይ አላህ በታላቅ ምንዳ አበለጠ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከምእመናን የጉዳት ባለቤት ከኾኑት በቀር ተቀማጮቹና በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የሚታገሉት አይተካከሉም፡፡ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የሚታገሉትን አላህ በተቀማጮቹ ላይ በደረጃ አበለጠ፡፡ ለሁሉም አላህ መልካሚቱን (ገነት) ተስፋ ሰጠ፡፡ ታጋዮቹንም በተቀማጮቹ ላይ አላህ በታላቅ ምንዳ አበለጠ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70