فَمَا لَكُمْ فِى ٱلْمُنَٰفِقِينَ فِئَتَيْنِ وَٱللَّهُ أَرْكَسَهُم بِمَا كَسَبُوٓا۟ أَتُرِيدُونَ أَن تَهْدُوا۟ مَنْ أَضَلَّ ٱللَّهُ وَمَن يُضْلِلِ ٱللَّهُ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ سَبِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy88.(አማኞች ሆይ) አላህ በስራዎቻቸው ምክንያት ወደ ክህደት የመለሳቸው ሲሆኑ በሙናፊቆች ጉዳይ እናንተ ለሁለት ቡድን የተከፈላችሁት ምን ሆናችሁ ነው? አላህ ያጠመመውን ሰው ልታቀኑ ታስባላችሁን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያጠመመውን ሰው ለእርሱ መንገድ ፈጽሞ አታገኝለትም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበመናፍቃንም (ነገር) አላህ በሥራዎቻቸው ወደ ክህደት የመለሳቸው ሲኾኑ ሁለት ክፍሎች የኾናችሁት ለናንተ ምን አላችሁ አላህ ያጠመመውን ሰው ልታቀኑ ታስባላችሁን አላህ ያሳሳተውን ሰው ለእርሱ መንገድን ፈጽሞ አታገኝለትም፡፡