ٱلرِّجَالُ قَوَّٰمُونَ عَلَى ٱلنِّسَآءِ بِمَا فَضَّلَ ٱللَّهُ بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ وَبِمَآ أَنفَقُوا۟ مِنْ أَمْوَٰلِهِمْ فَٱلصَّٰلِحَٰتُ قَٰنِتَٰتٌ حَٰفِظَٰتٌ لِّلْغَيْبِ بِمَا حَفِظَ ٱللَّهُ وَٱلَّٰتِى تَخَافُونَ نُشُوزَهُنَّ فَعِظُوهُنَّ وَٱهْجُرُوهُنَّ فِى ٱلْمَضَاجِعِ وَٱضْرِبُوهُنَّ فَإِنْ أَطَعْنَكُمْ فَلَا تَبْغُوا۟ عَلَيْهِنَّ سَبِيلًا إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيًّا كَبِيرًا
Amharic Translation - Africa Academy34. ወንዶች ለሴቶች ቋሚና የበላይ አስተዳዳሪዎች ናቸው:: አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና ወንዶች ከገንዘቦቻቸው ለሴቶች በመስጠታቸው ምክኒያት ነው:: መልካሞቹ ሴቶች ማለት ለባሎቻቸው ታዛዦች፤ አላህ ባስጠበቀው ነገር ከባሎቻቸው ሩቅ የሆነውን ጠባቂዎች ናቸው:: እነዚያን ማመፃቸውን የምትፈሩትን ሴቶች መጀመሪያ ገስጿቸው:: ከዚያም በመኝታቸው ተለዩዋቸው:: ከዚያም (በአካሎቻቸው ላይ ሳካ ሳታደርሱ) ምቷቸው:: ከታዘዟችሁ ለመጨቆን ስትሉ በእነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ:: አላህ የሁሉም በላይና ታላቅ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው፡፡ አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘቦቻቸው (ለሴቶች) በመስጠታቸው ነው፡፡ መልካሞቹም ሴቶች (ለባሎቻቸው) ታዛዦች አላህ ባስጠበቀው ነገር ሩቅን ጠባቂዎች ናቸው፡፡ እነዚያንም ማመጸቸውን የምትፈሩትን ገስጹዋቸው፡፡ በመኝታዎችም ተለዩዋቸው፡፡ (ሳካ ሳታደርሱ) ምቱዋቸውም፡፡ ቢታዘዟችሁም (ለመጨቆን) በእነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ፤ አላህ የበላይ ታላቅ ነውና፡፡