caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Nisaa፣ አንቀጽ 19

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 92 · 4:19

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا يَحِلُّ لَكُمْ أَن تَرِثُوا۟ ٱلنِّسَآءَ كَرْهًا وَلَا تَعْضُلُوهُنَّ لِتَذْهَبُوا۟ بِبَعْضِ مَآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ إِلَّآ أَن يَأْتِينَ بِفَٰحِشَةٍ مُّبَيِّنَةٍ وَعَاشِرُوهُنَّ بِٱلْمَعْرُوفِ فَإِن كَرِهْتُمُوهُنَّ فَعَسَىٰٓ أَن تَكْرَهُوا۟ شَيْـًٔا وَيَجْعَلَ ٱللَّهُ فِيهِ خَيْرًا كَثِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy19. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሴቶችን ያስገደዳችሁ ሆናችሁ ልትወርሱና ግልጽ የሆነ መጥፎ ስራ ካልሰሩ በስተቀር ከሰጣችኋቸው ከፊሉን ልትወስዱባቸውና ልታጉላሏዋቸው አይፈቀድላችሁም:: በመልካም ተኗኗሯቸው:: ብትጠሏቸዉም እንኳን ታገሱ:: አንድ ነገር ብትጠሉትም አላህ በእርሱ ዉስጥ ብዙ ደግ ነገሮችን ሊያደርግላችሁ ይችላልና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! ሴቶችን ያስገደዳችሁ ኾናችሁ ልትወርሱና ግልጽን መጥፎ ሥራ ካልሠሩ በስተቀር ከሰጣችኋቸው ከፊሉን ልትወስዱ ልታጉላሏቸውም ለእናንተ አይፈቀድም፡፡ በመልካምም ተኗኗሩዋቸው፡፡ ብትጠሉዋቸውም (ታገሱ)፡፡ አንዳችን ነገር ብትጠሉ አላህም በእርሱ ውስጥ ብዙ ደግ ነገርን ሊያደርግ ይቻላልና፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70