ሱረቱ Al-Maaida المائدة
120 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 112
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَوْفُوا۟ بِٱلْعُقُودِ أُحِلَّتْ لَكُم بَهِيمَةُ ٱلْأَنْعَٰمِ إِلَّا مَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ غَيْرَ مُحِلِّى ٱلصَّيْدِ وَأَنتُمْ حُرُمٌ إِنَّ ٱللَّهَ يَحْكُمُ مَا يُرِيدُ
Amharic Translation - Africa Academy1. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ቃልኪዳኖቻችሁን ሙሉ:: በእናንተ ላይ የሚነበበው ብቻ ሲቀር የግመል፤ የከብት፤ የበግና የፍየል እንስሳት ተፈቅዶላችኋል:: በሐጅ ስራ ላይ ሆናችሁ አውሬ ማደንን እንደ ተፈቀደ ሳትቆጥሩ የሚበሉት የዱር እንስሳትም ተፈቅደውላችኋል:: አላህ የሚፈልገውን ሁሉ ነገር ይፈርዳልና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تُحِلُّوا۟ شَعَٰٓئِرَ ٱللَّهِ وَلَا ٱلشَّهْرَ ٱلْحَرَامَ وَلَا ٱلْهَدْىَ وَلَا ٱلْقَلَٰٓئِدَ وَلَآ ءَآمِّينَ ٱلْبَيْتَ ٱلْحَرَامَ يَبْتَغُونَ فَضْلًا مِّن رَّبِّهِمْ وَرِضْوَٰنًا وَإِذَا حَلَلْتُمْ فَٱصْطَادُوا۟ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَـَٔانُ قَوْمٍ أَن صَدُّوكُمْ عَنِ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ أَن تَعْتَدُوا۟ وَتَعَاوَنُوا۟ عَلَى ٱلْبِرِّ وَٱلتَّقْوَىٰ وَلَا تَعَاوَنُوا۟ عَلَى ٱلْإِثْمِ وَٱلْعُدْوَٰنِ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ
Amharic Translation - Africa Academy2. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ምልክቶች ይሆኑ ዘንድ የከለከላቸውን ነገሮች የተፈቀዱ አታድርጉ። የተከበረውንም ወር በውስጡ ጦርነትን በማካሄድ አትድፈሩት:: ወደ መካ የሚነዱትን የመስዋዕት እንስሳትና የሚታበቱባቸውን ገመዶች፤ ከጌታቸው ችሮታንና ውዴታን ፈልገው ወደ ተከበረው ቤት አሳቢዎችንም በክፉ አትንኳቸው:: የሐጅን ስራ ፈጽማችሁ ባጠናቀቃችሁ ጊዜ የዱር አውሬዎችን እንደልባችሁ አድኑ:: ከተከበረው መስጊድ ስለከለከሏችሁ ሰዎችን መጥላታችሁ በእነርሱ ላይ ወሰንን እንድታልፉና ፍትህን እንድታዛቡ አይገፋፉችሁ:: በበጎ ተግባርና አላህን በመፍራት እርስ በእርስ ተባበሩ:: ኃጢአትና ወሰንን በማለፍ ግን አትተባበሩ:: አላህን በትክክል ፍሩ:: አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
حُرِّمَتْ عَلَيْكُمُ ٱلْمَيْتَةُ وَٱلدَّمُ وَلَحْمُ ٱلْخِنزِيرِ وَمَآ أُهِلَّ لِغَيْرِ ٱللَّهِ بِهِۦ وَٱلْمُنْخَنِقَةُ وَٱلْمَوْقُوذَةُ وَٱلْمُتَرَدِّيَةُ وَٱلنَّطِيحَةُ وَمَآ أَكَلَ ٱلسَّبُعُ إِلَّا مَا ذَكَّيْتُمْ وَمَا ذُبِحَ عَلَى ٱلنُّصُبِ وَأَن تَسْتَقْسِمُوا۟ بِٱلْأَزْلَٰمِ ذَٰلِكُمْ فِسْقٌ ٱلْيَوْمَ يَئِسَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِن دِينِكُمْ فَلَا تَخْشَوْهُمْ وَٱخْشَوْنِ ٱلْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِى وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلْإِسْلَٰمَ دِينًا فَمَنِ ٱضْطُرَّ فِى مَخْمَصَةٍ غَيْرَ مُتَجَانِفٍ لِّإِثْمٍ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy3. (ስዎች ሆይ!) በክት፤ ደም፤ የአሳማ ስጋ፤ ሲታረድ ከአላህ ስም ሌላ የተወሳበት እንሰሳ፤ ታንቃ የሞተች፤ ተደብድባ የተገደለች፤ ተንከባላ የሞተች፤ በቀንድ ተወግታ የሞተችና አውሬ የበላት ከእነዚህ በሕይወት ላይ እያሉ ደርሳችሁ ያረዳችሁት ብቻ ሲቀር ለጣዖታት የታረደና በአዝላም እድልን መፈለጋችሁ በእናንተ ላይ እርም ተደረገ:: እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን መፈጸም አላህን ማመጽ ነው:: ዛሬ እነዚያ በአላህ የካዱት ከሀይማኖታችሁ ተስፋ ቆረጡ:: ስለዚህ አትፍሩዋቸው:: ይልቁን እኔን ብቻ ፍሩኝ:: ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ:: ጸጋየንም በእናንተ ላይ ፈጸምኩ:: ለእናንተም በሃይማኖትነት ኢስላምን ወደድኩላችሁ:: በርሀብ ወቅት ወደ ኃጢአት ያዘነበለ ሳይሆን እርም የሆኑትን ነገሮች ለመብላት የተገደደ ሰው ሁሉ ለሕይወቱ ማቆያ ያህል ቢበላ ምንም ችግር የለበትም:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَسْـَٔلُونَكَ مَاذَآ أُحِلَّ لَهُمْ قُلْ أُحِلَّ لَكُمُ ٱلطَّيِّبَٰتُ وَمَا عَلَّمْتُم مِّنَ ٱلْجَوَارِحِ مُكَلِّبِينَ تُعَلِّمُونَهُنَّ مِمَّا عَلَّمَكُمُ ٱللَّهُ فَكُلُوا۟ مِمَّآ أَمْسَكْنَ عَلَيْكُمْ وَٱذْكُرُوا۟ ٱسْمَ ٱللَّهِ عَلَيْهِ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ سَرِيعُ ٱلْحِسَابِ
Amharic Translation - Africa Academy4.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ሙስሊሞች ) ምን ምን እንደተፈቀደላቸው ይጠይቁሃል:: «ለእናንተ መልካሞች ሁሉ እና እነዚያም አላህ ካሳወቃችሁ አሰልጣኞች ሆናችሁ ያስተማራችኋቸው አዳኞች ውሾች ያደኑት ሁሉ ተፈቀደላችሁ።» በላቸው:: አላህ ካስተማራችሁ እውቀት ታስተምሯቸዋላችሁ:: ከያዙላችሁ ነገር ብሉ:: የአላህንም ስምም አውሱበት:: አላህን ፍሩ:: አላህ ምርመራው ፈጣን ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلْيَوْمَ أُحِلَّ لَكُمُ ٱلطَّيِّبَٰتُ وَطَعَامُ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ حِلٌّ لَّكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّ لَّهُمْ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَٰفِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِىٓ أَخْدَانٍ وَمَن يَكْفُرْ بِٱلْإِيمَٰنِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُۥ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy5. (አማኞች ሆይ!) ዛሬ መልካም ነገሮች ለእናንተ ተፈቀዱ:: የእነዚያ መጽሐፍን የተሰጡ ሰዎች ምግብም (እርድ) ለእናንተ የተፈቀደ ነው:: ምግባችሁም ለእነርሱ የተፈቀደ ነው:: ከምዕመናት ሴቶችም ጥብቆቹ፤ ከእነዚያ ከናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡ ህዝቦች ሴቶችም መካከል ጥብቆቹ፤ ዝሙተኞችና የሚስጥር ወዳጅ ያዢዎች ሳትሆኑ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ ልታገቧቸው የተፈቀዱ ናቸው:: በአላህ ካመነ በኋላ ከእምነቱ ወደ ክህደት የሚመለስ ሁሉ በእርግጥ ስራው ተበላሸ:: በመጨረሻም ቀን ከከሳሪዎች ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِذَا قُمْتُمْ إِلَى ٱلصَّلَوٰةِ فَٱغْسِلُوا۟ وُجُوهَكُمْ وَأَيْدِيَكُمْ إِلَى ٱلْمَرَافِقِ وَٱمْسَحُوا۟ بِرُءُوسِكُمْ وَأَرْجُلَكُمْ إِلَى ٱلْكَعْبَيْنِ وَإِن كُنتُمْ جُنُبًا فَٱطَّهَّرُوا۟ وَإِن كُنتُم مَّرْضَىٰٓ أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ أَوْ جَآءَ أَحَدٌ مِّنكُم مِّنَ ٱلْغَآئِطِ أَوْ لَٰمَسْتُمُ ٱلنِّسَآءَ فَلَمْ تَجِدُوا۟ مَآءً فَتَيَمَّمُوا۟ صَعِيدًا طَيِّبًا فَٱمْسَحُوا۟ بِوُجُوهِكُمْ وَأَيْدِيكُم مِّنْهُ مَا يُرِيدُ ٱللَّهُ لِيَجْعَلَ عَلَيْكُم مِّنْ حَرَجٍ وَلَٰكِن يُرِيدُ لِيُطَهِّرَكُمْ وَلِيُتِمَّ نِعْمَتَهُۥ عَلَيْكُمْ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy6. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወደ ሶላት ለመግባት ባሰባችሁ ጊዜ ፊቶቻችሁንና እጆቻችሁን እስከ ክርኖቻችሁ ድረስ እጠቡ:: ራሶቻችሁንም በውሃ አብሱ:: እግሮቻችሁን እስከ ቁርጭምጭሚቶች እጠቡ:: ጀናባ ከሆናችሁ ሙሉ ገላችሁን ታጠቡ:: በሽተኞች ወይም በጉዞ ላይ ብትሆኑ ወይም ከናንተ አንዳችሁ ከዓይነ ምድር ቢወጣ ወይም ሴቶችን ብትነኩና (የግብረ ስጋ ግንኙነት ብትፈጽሙና) ውሃን ባታገኙ በንጹህ የምድር አፈር ተይሙም አድርጉ:: ከዚያም ከእርሱ ፊታችሁንና እጆቻችሁን አብሱ:: አላህ በእናንተ ላይ ምንንም ችግር ሊያደርግ አይሻምና:: ይልቁንም አላህን ታመሰግኑት ዘንድ ሊያጠራችሁና ጸጋውን በእናንተ ላይ ሊሞላ ይፈልጋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱذْكُرُوا۟ نِعْمَةَ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْ وَمِيثَٰقَهُ ٱلَّذِى وَاثَقَكُم بِهِۦٓ إِذْ قُلْتُمْ سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
Amharic Translation - Africa Academy7. በእናንተ ላይ የለገሰውን የአላህን ጸጋና ያንንም «ሰምተናል ታዘናልም» ባላችሁ ጊዜ ያጠበቀባችሁን ቃል ኪዳኑን አስታውሱ:: አላህንም ፍሩ:: አላህ በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُونُوا۟ قَوَّٰمِينَ لِلَّهِ شُهَدَآءَ بِٱلْقِسْطِ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَـَٔانُ قَوْمٍ عَلَىٰٓ أَلَّا تَعْدِلُوا۟ ٱعْدِلُوا۟ هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِيرٌۢ بِمَا تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy8. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ የቆማችሁ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ሁኑ:: ሕዝቦችንም መጥላታችሁ ላለማስተካከል አይገፋፋችሁ ፍትሀዊ ሁኑ:: ማስተካከል ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው:: አላህን ፍሩ:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَأَجْرٌ عَظِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy9. እነዚያ በአላህ ያመኑና በጎ ስራዎችን የሰሩ ሁሉ (አላህ ገነትን ቃል ገባላቸው::) ለእነርሱ ምህረትና ታላቅ ምንዳ አለላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَكَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَآ أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلْجَحِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy10. እነዚያ በአላህ የካዱና በአናቅጻችን ያስተባበሉ ሁሉ የእሳት ጓዶች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱذْكُرُوا۟ نِعْمَتَ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ هَمَّ قَوْمٌ أَن يَبْسُطُوٓا۟ إِلَيْكُمْ أَيْدِيَهُمْ فَكَفَّ أَيْدِيَهُمْ عَنكُمْ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ ٱلْمُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy11. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሕዝቦች እጆቻቸውን ለጥቃት ወደ እናንተ ሊዘረጉ ባሰቡና እጆቻቸውን ከናንተ ላይ በከለከለላችሁ ጊዜ ለእናንተ የዋለላችሁን ጸጋ አስታውሱ:: አላህንም ፍሩ። አማኞች በአላህ ላይ ብቻ ይመኩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ أَخَذَ ٱللَّهُ مِيثَٰقَ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ وَبَعَثْنَا مِنْهُمُ ٱثْنَىْ عَشَرَ نَقِيبًا وَقَالَ ٱللَّهُ إِنِّى مَعَكُمْ لَئِنْ أَقَمْتُمُ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَيْتُمُ ٱلزَّكَوٰةَ وَءَامَنتُم بِرُسُلِى وَعَزَّرْتُمُوهُمْ وَأَقْرَضْتُمُ ٱللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا لَّأُكَفِّرَنَّ عَنكُمْ سَيِّـَٔاتِكُمْ وَلَأُدْخِلَنَّكُمْ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ فَمَن كَفَرَ بَعْدَ ذَٰلِكَ مِنكُمْ فَقَدْ ضَلَّ سَوَآءَ ٱلسَّبِيلِ
Amharic Translation - Africa Academy12. አላህ የኢስራኢል ልጆችን የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዘባቸው:: ከእነርሱም መካከል አስራ ሁለት አለቆችን አስነሳን:: አላህም አላቸው፡- «ከእናንተ ጋር ነኝ። ሶላትን ደንቡን ጠብቃችሁ ብትሰግዱ፤ ግዴታ ምጽዋትንም በትክክል ብትሰጡ፤ በመልዕክተኞቼም በሙሉ ብታምኑና በሚያደርጉት ትግል ብትረዷቸው፤ ለአላህ መልካም ብድርን ብታበድሩ ኃጢአቶቻችሁንም አብስላችኋለሁ:: ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶችም በእርግጥ አስገባችኋለሁ:: ከዚህ በኋላ ከናንተ መካከል በአላህ የካደ ግን ከቀጥተኛው መንገድ ተሳሳተ::»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَبِمَا نَقْضِهِم مِّيثَٰقَهُمْ لَعَنَّٰهُمْ وَجَعَلْنَا قُلُوبَهُمْ قَٰسِيَةً يُحَرِّفُونَ ٱلْكَلِمَ عَن مَّوَاضِعِهِۦ وَنَسُوا۟ حَظًّا مِّمَّا ذُكِّرُوا۟ بِهِۦ وَلَا تَزَالُ تَطَّلِعُ عَلَىٰ خَآئِنَةٍ مِّنْهُمْ إِلَّا قَلِيلًا مِّنْهُمْ فَٱعْفُ عَنْهُمْ وَٱصْفَحْ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy13. ቃል ኪዳናቸውን በማፍረሳቸው ረገምናቸው:: ልቦቻቸውንም ደረቆች አደረግን:: ቃላትን ከቦታዎቻቸው ይለውጣሉ:: ከታዘዙትም ነገር ከፊሉን ተው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ጥቂቶቹ ሲቀሩ ክዳትን ከማየት አትወገድም:: ለእነርሱ ይቅርታ አድርግ:: እለፋቸዉም:: አላህ መልካም ሰሪዎችን ሁሉ ይወዳልና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّا نَصَٰرَىٰٓ أَخَذْنَا مِيثَٰقَهُمْ فَنَسُوا۟ حَظًّا مِّمَّا ذُكِّرُوا۟ بِهِۦ فَأَغْرَيْنَا بَيْنَهُمُ ٱلْعَدَاوَةَ وَٱلْبَغْضَآءَ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ وَسَوْفَ يُنَبِّئُهُمُ ٱللَّهُ بِمَا كَانُوا۟ يَصْنَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy14. ከእነዚያም «እኛ ክርስቲያኖች ነን» ካሉት ክፍሎች መካከል የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን:: ሆኖም ከታዘዙበት ነገር ከፊሉን ተው:: ስለዚህም እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብንና ጥላቻን ጣልንባቸው:: አላህም ይሰሩት የነበሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ قَدْ جَآءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَيَعْفُوا۟ عَن كَثِيرٍ قَدْ جَآءَكُم مِّنَ ٱللَّهِ نُورٌ وَكِتَٰبٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy15. እናንተ የመጽሐፍ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ መካከል ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ብዙውንም የሚተው ሲሆን መልዕክተኛችን ሙሐመድ መጣላችሁ:: ከአላህ ዘንድም ብርሃንና ገላጭ የሆነ መጽሐፍ መጣላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَهْدِى بِهِ ٱللَّهُ مَنِ ٱتَّبَعَ رِضْوَٰنَهُۥ سُبُلَ ٱلسَّلَٰمِ وَيُخْرِجُهُم مِّنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِ بِإِذْنِهِۦ وَيَهْدِيهِمْ إِلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy16. አላህ ውዴታውን የተከተሉትን ሁሉ የሰላምን መንገዶች በእርሱ ይመራበታል:: በፈቃዱም ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል:: ወደ ቀጥተኛዉም መንገድ ይመራቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَّقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَ قُلْ فَمَن يَمْلِكُ مِنَ ٱللَّهِ شَيْـًٔا إِنْ أَرَادَ أَن يُهْلِكَ ٱلْمَسِيحَ ٱبْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُۥ وَمَن فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًا وَلِلَّهِ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا يَخْلُقُ مَا يَشَآءُ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ «አላህ ማለት የመርየም ልጅ አልመሲህ ነው።» ያሉ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ በአላህ ካዱ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ የመርየምን ልጅ አልመሲህንና እናቱን እንደዚሁም በምድር ያለን ፍጡር ሁሉ ለማጥፋት ቢሻ ከአላህ ማዳን የሚችል ማን ነው? የሰማያትና የምድር የመካከላቸዉም ንግስና የአላህ ብቻ ነው:: የሚፈልገውን ይፈጥራል:: አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَتِ ٱلْيَهُودُ وَٱلنَّصَٰرَىٰ نَحْنُ أَبْنَٰٓؤُا۟ ٱللَّهِ وَأَحِبَّٰٓؤُهُۥ قُلْ فَلِمَ يُعَذِّبُكُم بِذُنُوبِكُم بَلْ أَنتُم بَشَرٌ مِّمَّنْ خَلَقَ يَغْفِرُ لِمَن يَشَآءُ وَيُعَذِّبُ مَن يَشَآءُ وَلِلَّهِ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا وَإِلَيْهِ ٱلْمَصِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy18. አይሁድና ክርስቲያኖች «እኛ የአላህ ልጆችና ወዳጆቹ ነን።» አሉ። «ታዲያ በኃጢአቶቻችሁ ለምን ይቀጣችኋል? አይደላችሁም:: እናንተ ከፈጠራቸው መካከል የሆናችሁ ሰዎች ናችሁ:: አላህ ለሚሻው ይምራል:: የሚሻውን ይቀጣል:: የሰማያትና የምድር በመካከላቸዉም ያለው ሁሉ ንግስናው የአላህ ብቻ ነው:: መመለሻም ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ قَدْ جَآءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ عَلَىٰ فَتْرَةٍ مِّنَ ٱلرُّسُلِ أَن تَقُولُوا۟ مَا جَآءَنَا مِنۢ بَشِيرٍ وَلَا نَذِيرٍ فَقَدْ جَآءَكُم بَشِيرٌ وَنَذِيرٌ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy19. እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! «አብሳሪና አስፈራሪ አልመጣልንም።» እንዳትሉ መልዕክተኞቻችን በተቋረጡበት ጊዜ መመሪያዎችን የሚያብራራ ሆኖ መልዕክተኛችን ሙሐመድ በእርግጥ መጣላችሁ:: አብሳሪና አስፈራሪም በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِۦ يَٰقَوْمِ ٱذْكُرُوا۟ نِعْمَةَ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَعَلَ فِيكُمْ أَنۢبِيَآءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكًا وَءَاتَىٰكُم مَّا لَمْ يُؤْتِ أَحَدًا مِّنَ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy20. ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን በእናንተ ላይ የዋለውን ጸጋ አስታውሱ፣ በውስጣችሁ ነብያትን ባደረገ፤ ነገስታትም ባደረጋችሁና ከአለማት ህዝብ ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰقَوْمِ ٱدْخُلُوا۟ ٱلْأَرْضَ ٱلْمُقَدَّسَةَ ٱلَّتِى كَتَبَ ٱللَّهُ لَكُمْ وَلَا تَرْتَدُّوا۟ عَلَىٰٓ أَدْبَارِكُمْ فَتَنقَلِبُوا۟ خَٰسِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy21. ‹‹ሕዝቦቼ ሆይ! ያችን አላህ ለእናንተ ያደረጋትን የተቀደሰችውን መሬት ግቡ:: ወደ ኋላችሁም አትመለሱ:: ከሳሪዎች ሆናችሁ ትመለሳላችሁና›› (ባሉ ጊዜ የሆነዉን አስታውስ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ يَٰمُوسَىٰٓ إِنَّ فِيهَا قَوْمًا جَبَّارِينَ وَإِنَّا لَن نَّدْخُلَهَا حَتَّىٰ يَخْرُجُوا۟ مِنْهَا فَإِن يَخْرُجُوا۟ مِنْهَا فَإِنَّا دَٰخِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy22. «ሙሳ ሆይ! በእርሷ ውስጥ ሀያላን ህዝቦች ስላሉ ከእርሷ እስከሚወጡ ድረስ ፈጽሞ አንገባትም:: ከወጡ ግን ገቢዎች ነን።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ رَجُلَانِ مِنَ ٱلَّذِينَ يَخَافُونَ أَنْعَمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِمَا ٱدْخُلُوا۟ عَلَيْهِمُ ٱلْبَابَ فَإِذَا دَخَلْتُمُوهُ فَإِنَّكُمْ غَٰلِبُونَ وَعَلَى ٱللَّهِ فَتَوَكَّلُوٓا۟ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy23. ከእነዚያ አላህን ከሚፈሩትና አላህ ጸጋውን ከለገሰላቸው ሰዎች መካከል ሁለት ሰዎች «በእነርሱ በሀያሎቹ ላይ በሩን ግቡ:: በገባችሁ ጊዜ እናንተ አሸናፊዎች ናችሁ:: ትክክለኛ አማኞችም እንደሆናችሁ በአላህ ላይ ብቻ ተመኩ።» አሏቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ يَٰمُوسَىٰٓ إِنَّا لَن نَّدْخُلَهَآ أَبَدًا مَّا دَامُوا۟ فِيهَا فَٱذْهَبْ أَنتَ وَرَبُّكَ فَقَٰتِلَآ إِنَّا هَٰهُنَا قَٰعِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy24. «ሙሳ ሆይ! እነርሱ በውስጧ እስካሉ ድረስ ፈጽሞ ምንጊዜም አንገባም:: ስለዚህ አንተና ጌታህ ሂዱና ተዋጉ:: እኛ እዚህ ተቀማጮች ነን።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ رَبِّ إِنِّى لَآ أَمْلِكُ إِلَّا نَفْسِى وَأَخِى فَٱفْرُقْ بَيْنَنَا وَبَيْنَ ٱلْقَوْمِ ٱلْفَٰسِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy25. ሙሳም «ጌታዬ ሆይ! እኔ ራሴንና ወንድሜን እንጂ ማንንም ላስገድድ አልችልም። ስለዚህ በእኛና በአመጸኞቹ ሕዝቦች መካከል ተገቢ ፍርድህን ስጥ።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فَإِنَّهَا مُحَرَّمَةٌ عَلَيْهِمْ أَرْبَعِينَ سَنَةً يَتِيهُونَ فِى ٱلْأَرْضِ فَلَا تَأْسَ عَلَى ٱلْقَوْمِ ٱلْفَٰسِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy26. አላህም: «ያቺ የተቀደሰችው መሬት በእነርሱ ላይ ለአርባ አመት ያህል እርም ናት። በምድረ በዳ ይንከራተታሉ። (ሙሳ ሆይ!) በአመጸኞችም ሕዝቦች ላይ አትዘን።» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ ٱبْنَىْ ءَادَمَ بِٱلْحَقِّ إِذْ قَرَّبَا قُرْبَانًا فَتُقُبِّلَ مِنْ أَحَدِهِمَا وَلَمْ يُتَقَبَّلْ مِنَ ٱلْـَٔاخَرِ قَالَ لَأَقْتُلَنَّكَ قَالَ إِنَّمَا يَتَقَبَّلُ ٱللَّهُ مِنَ ٱلْمُتَّقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱ ላይ የአደምን ሁለት ልጆች ወሬ (ማለትም) ሁለቱም ቁርባን ባቀረቡና አላህ ከአንደኛቸው ቁርባኑን ተቀብሎ ከሌላው ባልተቀበለበት ጊዜ የሆነውን ታሪክ አንብብላቸው:: ተቀባይነት ያጣው ወንድሙን «እገድልሃለሁ።» አለው። (የተዛተበትም) አለ: «አላህ የሚቀበለው እኮ ከጥንቁቆቹ ብቻ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَئِنۢ بَسَطتَ إِلَىَّ يَدَكَ لِتَقْتُلَنِى مَآ أَنَا۠ بِبَاسِطٍ يَدِىَ إِلَيْكَ لِأَقْتُلَكَ إِنِّىٓ أَخَافُ ٱللَّهَ رَبَّ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy28. «ልትገድለኝ እጅህን ወደ እኔ ብትዘረጋ እንኳን እኔ ልገድልህ እጄን ወደ አንተ የምዘረጋ አይደለሁም:: እኔ የአለማቱን ጌታ አላህን እፈራለሁና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنِّىٓ أُرِيدُ أَن تَبُوٓأَ بِإِثْمِى وَإِثْمِكَ فَتَكُونَ مِنْ أَصْحَٰبِ ٱلنَّارِ وَذَٰلِكَ جَزَٰٓؤُا۟ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy29. «እኔ በኃጢአቴና በኃጢአትህ ወደ ጌታህ ልትመለስና ከእሳት ጓዶች አንዱ ልትሆን እሻለሁ:: ይህም የበደለኞች ቅጣት ነው።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَطَوَّعَتْ لَهُۥ نَفْسُهُۥ قَتْلَ أَخِيهِ فَقَتَلَهُۥ فَأَصْبَحَ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy30. ነፍሱም ወንድሙን መግደሉ አስቻላትና(አስዋበችለት) ገደለው። ከከሳሪዎችም ሆነ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَبَعَثَ ٱللَّهُ غُرَابًا يَبْحَثُ فِى ٱلْأَرْضِ لِيُرِيَهُۥ كَيْفَ يُوَٰرِى سَوْءَةَ أَخِيهِ قَالَ يَٰوَيْلَتَىٰٓ أَعَجَزْتُ أَنْ أَكُونَ مِثْلَ هَٰذَا ٱلْغُرَابِ فَأُوَٰرِىَ سَوْءَةَ أَخِى فَأَصْبَحَ مِنَ ٱلنَّٰدِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy31. ዘንድ አላህ መሬትን የሚጭር ቁራ ላከለት የወንድሙን ሬሳ እንዴት እንደሚቀብር ሊያሳየው። «ወይኔ የወንድሜን ሬሳ እቀብር ዘንድ እንደዚህ ቁራ መሆን እንኳን አቃተኝን?» አለ። ከዚያም ከጸጸተኞች ሆነ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مِنْ أَجْلِ ذَٰلِكَ كَتَبْنَا عَلَىٰ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ أَنَّهُۥ مَن قَتَلَ نَفْسًۢا بِغَيْرِ نَفْسٍ أَوْ فَسَادٍ فِى ٱلْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ ٱلنَّاسَ جَمِيعًا وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَآ أَحْيَا ٱلنَّاسَ جَمِيعًا وَلَقَدْ جَآءَتْهُمْ رُسُلُنَا بِٱلْبَيِّنَٰتِ ثُمَّ إِنَّ كَثِيرًا مِّنْهُم بَعْدَ ذَٰلِكَ فِى ٱلْأَرْضِ لَمُسْرِفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy32. በዚህ ምክንያት በኢስራኢል ልጆች ላይ «አንዲትን ንጹህ ነፍስን (ያልገደለችን) ወይም በምድር ላይ ምንንም ያላጠፋችን ነፍስ የገደለ ሁሉ ሰዎችን ሁሉ እንደገደለ ነው:: አንዲትን ነፍስ ህያው ያደረጋትም ሰዎችን ሁሉ ህያው እንዳደረገ ነው።» ማለትን ደነገግን። መልዕክተኞቻችንም ግልጽን ተዐምራት አምጥተውላቸዋል። ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ብዙዎቹ በምድር ላይ ወሰንን አላፊዎች ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّمَا جَزَٰٓؤُا۟ ٱلَّذِينَ يُحَارِبُونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَيَسْعَوْنَ فِى ٱلْأَرْضِ فَسَادًا أَن يُقَتَّلُوٓا۟ أَوْ يُصَلَّبُوٓا۟ أَوْ تُقَطَّعَ أَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُم مِّنْ خِلَٰفٍ أَوْ يُنفَوْا۟ مِنَ ٱلْأَرْضِ ذَٰلِكَ لَهُمْ خِزْىٌ فِى ٱلدُّنْيَا وَلَهُمْ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy33. የእነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን የሚዋጉ፤ በምድርም ላይ ለጥፋት የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ቅጣት መገደል ወይም መሰቀል ወይም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በማፈራረቅ መቆረጥ ወይም ከሀገር መባረር ነው:: ይህ ቅጣት ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት ነው:: በመጨረሻይቱም ዓለም ከባድ ቅጣት አለባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا ٱلَّذِينَ تَابُوا۟ مِن قَبْلِ أَن تَقْدِرُوا۟ عَلَيْهِمْ فَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy34. (ሙስሊሞች ሆይ!) (ይህ ተግባር የሚፈጸመው) እነዚያ በእነርሱ ላይ ከመቻላችሁ በፊት የተጸጸቱት ሲቀሩ (ነው)፤ አላህም መሀሪና አዛኝ መሆኑን እወቁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَٱبْتَغُوٓا۟ إِلَيْهِ ٱلْوَسِيلَةَ وَجَٰهِدُوا۟ فِى سَبِيلِهِۦ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy35. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ:: ወደ እርሱም የሚያቀርባችሁን ነገር ሁሉ ፈልጉ:: ትድኑ ዘንድም በእርሱ መንገድ ላይ ብቻ ታገሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَوْ أَنَّ لَهُم مَّا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًا وَمِثْلَهُۥ مَعَهُۥ لِيَفْتَدُوا۟ بِهِۦ مِنْ عَذَابِ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ مَا تُقُبِّلَ مِنْهُمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy36. እነዚያ የካዱት በምድር ላይ ያለ ነገርን ሁሉ እና ከርሱ ጋርም መሰሉ ተጨምሮላቸው ከትንሳኤ ቀን ቅጣት ነፃ ለመሆን እርሱን ቤዛ ቢሰጡ እንኳን ተቀባይነት አያገኙም። ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يُرِيدُونَ أَن يَخْرُجُوا۟ مِنَ ٱلنَّارِ وَمَا هُم بِخَٰرِجِينَ مِنْهَا وَلَهُمْ عَذَابٌ مُّقِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy37. ከእሳት ሊወጡ ይፈልጋሉ:: እነርሱ ግን ሁልጊዜም ከእርሷ ወጪዎች አይደሉም:: ለእነርሱ ዘውታሪ ቅጣት አለባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلسَّارِقُ وَٱلسَّارِقَةُ فَٱقْطَعُوٓا۟ أَيْدِيَهُمَا جَزَآءًۢ بِمَا كَسَبَا نَكَٰلًا مِّنَ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy38. የወንድ ሌባንና የሴት ሌባን ለሰሩት ወንጀል ከአላህ የሆነ መቀጫ ሲሆን እጆቻቸውን ቁረጡ:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَن تَابَ مِنۢ بَعْدِ ظُلْمِهِۦ وَأَصْلَحَ فَإِنَّ ٱللَّهَ يَتُوبُ عَلَيْهِ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy39. ከበደለ በኋላ የተጸጸተና ስራውን ያሳመረ ሁሉ አላህ ጸጸቱን ይቀበለዋል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ ٱللَّهَ لَهُۥ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ يُعَذِّبُ مَن يَشَآءُ وَيَغْفِرُ لِمَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና የእሱ ብቻ መሆኑን አላወክምን? የሚሻውን ሰው ይቀጣል:: ለሚሻውም ሰው ይምራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلرَّسُولُ لَا يَحْزُنكَ ٱلَّذِينَ يُسَٰرِعُونَ فِى ٱلْكُفْرِ مِنَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا بِأَفْوَٰهِهِمْ وَلَمْ تُؤْمِن قُلُوبُهُمْ وَمِنَ ٱلَّذِينَ هَادُوا۟ سَمَّٰعُونَ لِلْكَذِبِ سَمَّٰعُونَ لِقَوْمٍ ءَاخَرِينَ لَمْ يَأْتُوكَ يُحَرِّفُونَ ٱلْكَلِمَ مِنۢ بَعْدِ مَوَاضِعِهِۦ يَقُولُونَ إِنْ أُوتِيتُمْ هَٰذَا فَخُذُوهُ وَإِن لَّمْ تُؤْتَوْهُ فَٱحْذَرُوا۟ وَمَن يُرِدِ ٱللَّهُ فِتْنَتَهُۥ فَلَن تَمْلِكَ لَهُۥ مِنَ ٱللَّهِ شَيْـًٔا أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَمْ يُرِدِ ٱللَّهُ أَن يُطَهِّرَ قُلُوبَهُمْ لَهُمْ فِى ٱلدُّنْيَا خِزْىٌ وَلَهُمْ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy41. መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እነዚያ ወደ ክህደት የሚቻኮሉ ሆነው ልቦቻቸው ሳያምኑ በአፎቻቸው ብቻ «አመንን» ካሉት አስመሳዮችና ከእነዚያም አይሁዶቹ አያሳዝኑህ:: እነርሱ ውሸትን ብቻ አድማጮች ናቸውና:: ገና ወደ አንተ ላልመጡ ለሌሎች ሕዝቦች አድማጮች ናቸው:: ንግግሮችንም ከስፍሮቻቸው ወደ ሌላ በመቀየር መልዕክት ያጣምማሉ። «ይህንን የተጣመመውን ከተሰጣችሁ ያዙት:: ካልተሰጣችሁም ተጠንቀቁ።» ይላሉ:: አላህ መፈተንን የሚሻበትን ሰው ሁሉ ለእርሱ ከአላህ ለመከላከል ፍጹም አትችልም:: እነዚያ ማለት አላህ ልቦቻቸውን ማጥራትን ያልሻላቸው ሰዎች ናቸው:: ለእነርሱም በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አለባቸው:: ለእነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለምም ሌላ ከባድ ቅጣት አለባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
سَمَّٰعُونَ لِلْكَذِبِ أَكَّٰلُونَ لِلسُّحْتِ فَإِن جَآءُوكَ فَٱحْكُم بَيْنَهُمْ أَوْ أَعْرِضْ عَنْهُمْ وَإِن تُعْرِضْ عَنْهُمْ فَلَن يَضُرُّوكَ شَيْـًٔا وَإِنْ حَكَمْتَ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِٱلْقِسْطِ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلْمُقْسِطِينَ
Amharic Translation - Africa Academy42. እነርሱ ውሸትን አድማጮች፤ እርም የሆኑ ነገሮችን በላተኞች ናቸው:: እናም ለዳኝነት ወደ አንተ ዘንድ ከመጡ በመካከላቸው በትክክል ፍረድ። ወይም ተዋቸው:: ብትተዋቸው በምንም አይጎዱሁም:: ከፈረድክ ግን በመካከላቸው በትክክል ፍረድ:: አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَيْفَ يُحَكِّمُونَكَ وَعِندَهُمُ ٱلتَّوْرَىٰةُ فِيهَا حُكْمُ ٱللَّهِ ثُمَّ يَتَوَلَّوْنَ مِنۢ بَعْدِ ذَٰلِكَ وَمَآ أُو۟لَٰٓئِكَ بِٱلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy43. እነርሱ ዘንድ በውስጧ የአላህ ፍርድ ያለባት ተውራት እያለ እንዴት ያስፈርዱሃል? ከዚያ በኋላ ይሸሻሉ። እነዚያ በፍጹም ትክክለኛ አማኞች አይደሉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّآ أَنزَلْنَا ٱلتَّوْرَىٰةَ فِيهَا هُدًى وَنُورٌ يَحْكُمُ بِهَا ٱلنَّبِيُّونَ ٱلَّذِينَ أَسْلَمُوا۟ لِلَّذِينَ هَادُوا۟ وَٱلرَّبَّٰنِيُّونَ وَٱلْأَحْبَارُ بِمَا ٱسْتُحْفِظُوا۟ مِن كِتَٰبِ ٱللَّهِ وَكَانُوا۟ عَلَيْهِ شُهَدَآءَ فَلَا تَخْشَوُا۟ ٱلنَّاسَ وَٱخْشَوْنِ وَلَا تَشْتَرُوا۟ بِـَٔايَٰتِى ثَمَنًا قَلِيلًا وَمَن لَّمْ يَحْكُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْكَٰفِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy44. ተውራትን በውስጡ ለሰዎች መመሪያና ብርሃን ያለባት ሲሆን አወረድነው:: እነዚያ ትዕዛዙን የተቀበሉት ነብያት በአይሁዳውያን ላይ በእርሱ ይፈርዳሉ:: ሊቃውንቱና አዋቂዎቹም ከአላህ መጽሐፍን እንዲጠብቁ በተደረጉትና በእርሱ ላይ መስካሪዎቹ በመሆናቸው እንዲሁ በሱ ይፈርዳሉ:: እናም ሰዎችን አትፍሩ:: እኔን ብቻ ፍሩኝ:: በአንቀፆቼም አነስተኛን ዋጋ አትለውጡ አትግዙ:: እነዚያ አላህ ባወረደው መመሪያ ያልፈረዱ ሁሉ ከሓዲያን ማለት እነርሱው ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَتَبْنَا عَلَيْهِمْ فِيهَآ أَنَّ ٱلنَّفْسَ بِٱلنَّفْسِ وَٱلْعَيْنَ بِٱلْعَيْنِ وَٱلْأَنفَ بِٱلْأَنفِ وَٱلْأُذُنَ بِٱلْأُذُنِ وَٱلسِّنَّ بِٱلسِّنِّ وَٱلْجُرُوحَ قِصَاصٌ فَمَن تَصَدَّقَ بِهِۦ فَهُوَ كَفَّارَةٌ لَّهُۥ وَمَن لَّمْ يَحْكُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy45. በእነርሱም ላይ በውስጡ ነፍስን በነፍስ፤ አይንን በአይን፤ አፍንጫን በአፍንጫ፤ ጆሮን በጆሮ፤ ጥርስን በጥርስ፤ ይያዛል:: ቁስሎችንም ማመሳሰል አለባቸው ብለን ደነገግን:: ይህንን መብቱን ይቅር ያለ ሁሉ እርሱ ለኃጢአቱ ማሰረዣው ነው:: አላህ ባወረደው መመሪያ የማይፈርዱ ሁሉ እነዚያ በደለኞቹ ማለት እነርሱ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَفَّيْنَا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم بِعِيسَى ٱبْنِ مَرْيَمَ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلتَّوْرَىٰةِ وَءَاتَيْنَٰهُ ٱلْإِنجِيلَ فِيهِ هُدًى وَنُورٌ وَمُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلتَّوْرَىٰةِ وَهُدًى وَمَوْعِظَةً لِّلْمُتَّقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy46. በነብያቶች ፈለግ ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን በስተፊቱ ያለውን ተውራትን አረጋጋጭ ሲሆን አስከተልን:: ኢንጅልም በውስጡ ቀጥተኛ መመሪያና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለውን ተውራትን የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆቹም መሪና ገሳጭ ሲሆን ሰጠነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلْيَحْكُمْ أَهْلُ ٱلْإِنجِيلِ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فِيهِ وَمَن لَّمْ يَحْكُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْفَٰسِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy47. የኢንጂል ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ህግ ይፍረዱ:: አላህ ባወረደው የማይፈርዱ አመጸኞች ማለት እነርሱው ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ لِكُلٍّ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةً وَمِنْهَاجًا وَلَوْ شَآءَ ٱللَّهُ لَجَعَلَكُمْ أُمَّةً وَٰحِدَةً وَلَٰكِن لِّيَبْلُوَكُمْ فِى مَآ ءَاتَىٰكُمْ فَٱسْتَبِقُوا۟ ٱلْخَيْرَٰتِ إِلَى ٱللَّهِ مَرْجِعُكُمْ جَمِيعًا فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! )ከበፊቱ የነበረውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ አድርገን ባንተ ላይ ቁርኣንን አወረድን:: እናም በመካከላቸው አላህ ባወረደው ህግ ፍረድ:: እውነቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል:: ለሁላችሁም ህግንና መንገድን አደረግን:: አላህ በፈለገ ኖሮ አንድ ሕዝብ ባደረጋችሁ ነበር:: ግን በሰጣችሁ ሕግጋት ሊሞክራችሁ ነው ለእያንዳንዳችሁ መንገዶችን ያደረገው:: እናም በጎ ስራዎችን ለመስራት ተሽቀዳደሙ:: የሁላችሁም መመለሻ ወደ አላህ ብቻ ነው:: ከዚያ በእርሱ ትለያዩበት የነበራችሁትን ነገር እውነታ ይነግራችኋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنِ ٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ وَٱحْذَرْهُمْ أَن يَفْتِنُوكَ عَنۢ بَعْضِ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ إِلَيْكَ فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَٱعْلَمْ أَنَّمَا يُرِيدُ ٱللَّهُ أَن يُصِيبَهُم بِبَعْضِ ذُنُوبِهِمْ وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ ٱلنَّاسِ لَفَٰسِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመካከላቸው አላህ ባወረደው ህግ ፍረድ እንጂ ፈላጎቶቻቸውን አትከተል:: አላህ ወደ አንተ ካወረደው ከከፊሉ እንዳያሳስቱህ ተጠንቀቃቸው ማለትን አወረድን:: ከውሳኔው እምቢ ብለው ቢዞሩም አላህ የሚሻው በከፊሉ ኃጢአታቸው ሊቀጣቸው መሆኑን እወቅ:: ከሰዎቹ ብዙዎቹም አመጸኞች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَحُكْمَ ٱلْجَٰهِلِيَّةِ يَبْغُونَ وَمَنْ أَحْسَنُ مِنَ ٱللَّهِ حُكْمًا لِّقَوْمٍ يُوقِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy50. ለመሆኑ የመሀይምነትን ፍርድ ይፈልጋሉን? ለሚያረጋግጡ ህዝቦች ሁሉ ከአላህ ይበልጥ ፍርዱ ያማረ ማን ነው?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَتَّخِذُوا۟ ٱلْيَهُودَ وَٱلنَّصَٰرَىٰٓ أَوْلِيَآءَ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَآءُ بَعْضٍ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمْ فَإِنَّهُۥ مِنْهُمْ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy51. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አይሁድንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አታድርጓቸው:: ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸውና:: ከናንተ ውስጥ እነርሱን ረዳቶቹ (ወዳጆቹ) የሚያደርጋቸው ከእነርሱው ነው:: አላህ አመጸኞችን ህዝቦች አያቀናም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَتَرَى ٱلَّذِينَ فِى قُلُوبِهِم مَّرَضٌ يُسَٰرِعُونَ فِيهِمْ يَقُولُونَ نَخْشَىٰٓ أَن تُصِيبَنَا دَآئِرَةٌ فَعَسَى ٱللَّهُ أَن يَأْتِىَ بِٱلْفَتْحِ أَوْ أَمْرٍ مِّنْ عِندِهِۦ فَيُصْبِحُوا۟ عَلَىٰ مَآ أَسَرُّوا۟ فِىٓ أَنفُسِهِمْ نَٰدِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያን በልቦቻቸው ውስጥ የንፍቅና በሽታ ያለባቸውን ሰዎች «የጊዜ መለዋወጥ እንዳያገኘን እንፈራለን።» የሚሉ ሆነው አይሁድን ለመርዳት ሲቻኮሉ ታያቸዋለህ:: አላህ ድል መቀዳጀትን ወይም ከእርሱ ዘንድ የሆነን ነገር ሊያመጣና ከዚያ በነፍሶቻቸው ውስጥ በደበቁት ነገር ተጸፃቾች እንደሚሆኑ ይከጀላል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَقُولُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَهَٰٓؤُلَآءِ ٱلَّذِينَ أَقْسَمُوا۟ بِٱللَّهِ جَهْدَ أَيْمَٰنِهِمْ إِنَّهُمْ لَمَعَكُمْ حَبِطَتْ أَعْمَٰلُهُمْ فَأَصْبَحُوا۟ خَٰسِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy53. እነዚያ ያመኑት ሰዎች «እነዚያ ‹ከናንተ ጋር ነን› ብለው የጠነከረ መሀላቸውን በአላህ የማሉት እነዚህ ናቸውን?» ይላሉ:: ስራዎቻቸዉም ተበላሹ:: ከሳሪዎችም ሆኑ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مَن يَرْتَدَّ مِنكُمْ عَن دِينِهِۦ فَسَوْفَ يَأْتِى ٱللَّهُ بِقَوْمٍ يُحِبُّهُمْ وَيُحِبُّونَهُۥٓ أَذِلَّةٍ عَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ أَعِزَّةٍ عَلَى ٱلْكَٰفِرِينَ يُجَٰهِدُونَ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلَا يَخَافُونَ لَوْمَةَ لَآئِمٍ ذَٰلِكَ فَضْلُ ٱللَّهِ يُؤْتِيهِ مَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ وَٰسِعٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy54. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ውስጥ ከሃይማኖቱ ወደ ክህደት የሚመለስ ሁሉ አላህ በእርሱ ስፍራ የሚወዳቸውና የሚወዱትን በምዕምናን ላይ ትሁቶች፤ በከሓዲያን ላይ ሀያላን፤ የሆኑትንና በአላህ መንገድ የሚታገሉን የወቃሽንም ወቀሳ የማይፈሩ ህዝቦችን ያመጣል:: ይህ የአላህ ችሮታ ነው:: ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል:: አላህ ችሮታው ሰፊ ሁሉንም አዋቂ ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّمَا وَلِيُّكُمُ ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱلَّذِينَ يُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤْتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَهُمْ رَٰكِعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy55. (አማኞች ሆይ!) ረዳታችሁ አላህና መልዕክተኛው እንደዚሁም እነዚያ በአላህ ያመኑት ናቸው:: እነርሱ ማለት እነዚያ ሶላትን በደንቡ የሚሰግዱ እነርሱም (ለአምልኮ) የሚያጎነብሱ ሆነው ምጽዋትን የሚሰጡ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَن يَتَوَلَّ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ فَإِنَّ حِزْبَ ٱللَّهِ هُمُ ٱلْغَٰلِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy56. አላህን፤ መልዕክተኛውንና እንደዚሁ እነዚያ በአላህ ያመኑትን ሰዎች የሚወዳጅ (ከአላህ ጭፍሮች ይሆናል።) የአላህ ጭፍሮች ደግሞ አሸናፊዎቹ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَتَّخِذُوا۟ ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُوا۟ دِينَكُمْ هُزُوًا وَلَعِبًا مِّنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِكُمْ وَٱلْكُفَّارَ أَوْلِيَآءَ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy57. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ ከበፊታችሁ መጽሐፉን ከተሰጡትና ከእነዚያ ሃይማኖታችሁን መሳለቂያና መጫዎቻ ካደረጉት ከሓዲያን መካከል ወዳጆች አታድርጉ:: ትክክለኛ አማኞች እንደሆናችሁ አላህን ብቻ ፍሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا نَادَيْتُمْ إِلَى ٱلصَّلَوٰةِ ٱتَّخَذُوهَا هُزُوًا وَلَعِبًا ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy58. (ሙስሊሞች ሆይ!) ወደ ሶላት በጠራችሁም ጊዜ ጥሪዋን መሳለቂያና መጫዎቻ ያደርጓታል። ይህ እነርሱ የማያስተውሉ ህዝቦች በመሆናቸው ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ هَلْ تَنقِمُونَ مِنَّآ إِلَّآ أَنْ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيْنَا وَمَآ أُنزِلَ مِن قَبْلُ وَأَنَّ أَكْثَرَكُمْ فَٰسِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy59. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በአላህና ወደኛ በተወረደው በፊትም በተወረደው ለማመናችን አብዛኞቻችሁም አመጸኞች ለመኾናችሁ እንጅ (ሌላን ነገር) ከኛ ትጠላላችሁን?» በላቸው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ هَلْ أُنَبِّئُكُم بِشَرٍّ مِّن ذَٰلِكَ مَثُوبَةً عِندَ ٱللَّهِ مَن لَّعَنَهُ ٱللَّهُ وَغَضِبَ عَلَيْهِ وَجَعَلَ مِنْهُمُ ٱلْقِرَدَةَ وَٱلْخَنَازِيرَ وَعَبَدَ ٱلطَّٰغُوتَ أُو۟لَٰٓئِكَ شَرٌّ مَّكَانًا وَأَضَلُّ عَن سَوَآءِ ٱلسَّبِيلِ
Amharic Translation - Africa Academy60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ዘንድ ቅጣቱ ከዚህ ሁሉ የከፋን ነገር ልንገራችሁን?» በላቸው:: እርሱም «አላህ የረገማቸውና በእነርሱም ላይ የተቆጣባቸው ናቸው:: ከመካከላቸዉም ዝንጀሮዎችና ከርከሮዎች ያደረጋቸው ጣዖትንም የተገዙ ሰዎች ሃይማኖት ነው:: እነዚያ በጣም በከፋ ስፍራ ናቸው:: ከቀጥተኛዉም መንገድ በጣም የተሳሳቱ ናቸው።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا جَآءُوكُمْ قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا وَقَد دَّخَلُوا۟ بِٱلْكُفْرِ وَهُمْ قَدْ خَرَجُوا۟ بِهِۦ وَٱللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا كَانُوا۟ يَكْتُمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy61. ( አማኞች ሆይ!) ወደ እናንተ በመጡ ጊዜ ከክህደት ጋር ሁነው የገቡ ከእርሱ (ከክህደቱ) ጋር ሁነውም የወጡ ሲሆኑ ልክ እንደናንተ «አምነናል» ይላሉ:: አላህ ያንን ይደብቁት የነበረውን ነገር ሁሉ ጠንቅቆ አዋቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَتَرَىٰ كَثِيرًا مِّنْهُمْ يُسَٰرِعُونَ فِى ٱلْإِثْمِ وَٱلْعُدْوَٰنِ وَأَكْلِهِمُ ٱلسُّحْتَ لَبِئْسَ مَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy62. (መልዕክተኛችን መሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ ብዙዎቹን በኃጢአትና በበደል እርምንም የሆነ ለመብላት ሲጣደፉ ታያቸዋለህ:: ይሰሩት የነበረው በጣም ከፋ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَوْلَا يَنْهَىٰهُمُ ٱلرَّبَّٰنِيُّونَ وَٱلْأَحْبَارُ عَن قَوْلِهِمُ ٱلْإِثْمَ وَأَكْلِهِمُ ٱلسُّحْتَ لَبِئْسَ مَا كَانُوا۟ يَصْنَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy63. ቀሳውስቱና ሊቃውንቱ ከኃጢአት ንግግራቸውና እርምን ከመብላታቸው አይከለክሏቸዉም ኖሯልን? ይሰሩት የነበረው በጣም ከፋ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَتِ ٱلْيَهُودُ يَدُ ٱللَّهِ مَغْلُولَةٌ غُلَّتْ أَيْدِيهِمْ وَلُعِنُوا۟ بِمَا قَالُوا۟ بَلْ يَدَاهُ مَبْسُوطَتَانِ يُنفِقُ كَيْفَ يَشَآءُ وَلَيَزِيدَنَّ كَثِيرًا مِّنْهُم مَّآ أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ طُغْيَٰنًا وَكُفْرًا وَأَلْقَيْنَا بَيْنَهُمُ ٱلْعَدَٰوَةَ وَٱلْبَغْضَآءَ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ كُلَّمَآ أَوْقَدُوا۟ نَارًا لِّلْحَرْبِ أَطْفَأَهَا ٱللَّهُ وَيَسْعَوْنَ فِى ٱلْأَرْضِ فَسَادًا وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ ٱلْمُفْسِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy64. አይሁድ «የአላህ እጅ የታሰረ ነው።» አሉ:: እጆቻቸው ይታሰሩ:: ባሉትም ነገር ይረገሙ። ይልቁንም የአላህ ሁለቱም እጆቹ የተዘረጉ ናቸው:: እንደፈለገ ይለግሳል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው ቁርኣን ከእነርሱ መካከል ለብዙዎቹ ትዕቢትንና ክህደትን በእርግጥ ይጨምርባቸዋል:: በአይሁድ መካከል ጠብንና ጥላቻን እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ አደረግን:: ለጦር እሳትን ባቀጣጠሉ ቁጥር አላህ ያጠፋባቸዋል:: በምድር ውስጥ ለማበላሸት ይሮጣሉ:: አላህም አበላሾችን ሁሉ አይወድም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ أَنَّ أَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ ءَامَنُوا۟ وَٱتَّقَوْا۟ لَكَفَّرْنَا عَنْهُمْ سَيِّـَٔاتِهِمْ وَلَأَدْخَلْنَٰهُمْ جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy65. የመጽሐፉ ባለቤቶች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ ከእነርሱ ኃጢአቶቻቸውን በእርግጥ ባበስንና የመጠቀሚያ ገነቶችን በእርግጥ ባስገባናቸው ነበር።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ أَنَّهُمْ أَقَامُوا۟ ٱلتَّوْرَىٰةَ وَٱلْإِنجِيلَ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيْهِم مِّن رَّبِّهِمْ لَأَكَلُوا۟ مِن فَوْقِهِمْ وَمِن تَحْتِ أَرْجُلِهِم مِّنْهُمْ أُمَّةٌ مُّقْتَصِدَةٌ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ سَآءَ مَا يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy66. እነርሱ ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታቸው ወደ እነርሱ የተወረደውን መጽሐፍ በሰሩበት ኖሮ ከበላያቸውና ከእግሮቻቸው ስር በተመገቡ ነበር:: ከእነርሱ መካከል ትክክለኛ ህዝቦች አሉ:: ከእነርሱ መካከል ብዙዎቹ ግን የሚሰሩት ነገር ከፋ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلرَّسُولُ بَلِّغْ مَآ أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ وَإِن لَّمْ تَفْعَلْ فَمَا بَلَّغْتَ رِسَالَتَهُۥ وَٱللَّهُ يَعْصِمُكَ مِنَ ٱلنَّاسِ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy67. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ቁርኣን አድርስ:: ይህን ባትሰራ ግን የጌታህን መልዕክቱን አላደርስክም:: አላህም ከሰዎች (ተንኮል) ይጠብቅሃል:: አላህ ከሓዲያን ሕዝቦችን አያቀናም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَسْتُمْ عَلَىٰ شَىْءٍ حَتَّىٰ تُقِيمُوا۟ ٱلتَّوْرَىٰةَ وَٱلْإِنجِيلَ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ وَلَيَزِيدَنَّ كَثِيرًا مِّنْهُم مَّآ أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ طُغْيَٰنًا وَكُفْرًا فَلَا تَأْسَ عَلَى ٱلْقَوْمِ ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ የመጽሐፍ ባለቤቶች ሆይ! ተውራትን፤ ኢንጂልን እና ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ቁርኣንን እስከምትሰሩባቸው ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም።» በላቸው:: ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው ቁርኣን ከእነርሱ ብዙዎቹን ትዕቢትንና ክህደትን በእርግጥ ይጨምርባቸዋል:: በካሐዲያን ህዝቦች ላይ አትዘን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَٱلَّذِينَ هَادُوا۟ وَٱلصَّٰبِـُٔونَ وَٱلنَّصَٰرَىٰ مَنْ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَعَمِلَ صَٰلِحًا فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy69. እነዚያ ያመኑ፤ አይሁዳዊያን፤ ሳቢያኖችና ክርስቲያኖች ከእነርሱ መካከል በአላህና በመጨረሻው ቀን በትክክል ያመኑና መልካምን የሰሩ ሁሉ በእነርሱ ላይ ስጋት የለባቸዉም። አይተክዙምም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَقَدْ أَخَذْنَا مِيثَٰقَ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ وَأَرْسَلْنَآ إِلَيْهِمْ رُسُلًا كُلَّمَا جَآءَهُمْ رَسُولٌۢ بِمَا لَا تَهْوَىٰٓ أَنفُسُهُمْ فَرِيقًا كَذَّبُوا۟ وَفَرِيقًا يَقْتُلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy70. የኢስራኢል ልጆች የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዝንባቸው:: ወደ እነርሱም መልዕክተኞችን ላክን:: ነፍሶቻቸው በማትወደው ነገር መልዕክተኛ በመጣላቸው ቁጥር ከፊሉን አስተባበሉ:: ከፊሉንም ይገድላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَحَسِبُوٓا۟ أَلَّا تَكُونَ فِتْنَةٌ فَعَمُوا۟ وَصَمُّوا۟ ثُمَّ تَابَ ٱللَّهُ عَلَيْهِمْ ثُمَّ عَمُوا۟ وَصَمُّوا۟ كَثِيرٌ مِّنْهُمْ وَٱللَّهُ بَصِيرٌۢ بِمَا يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy71. በእነርሱ ላይ ፈተና አለመኖሩዋን ጠረጠሩምና ታወሩ ደነቆሩም:: ከዚያም አላህ ከእነርሱ ላይ ጸጸትን ተቀበለ:: ከዚያም ከእነርሱ ብዙዎቹ እንደገና ታወሩ ደነቆሩ:: አላህ የሚሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَ وَقَالَ ٱلْمَسِيحُ يَٰبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ إِنَّهُۥ مَن يُشْرِكْ بِٱللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ ٱلْجَنَّةَ وَمَأْوَىٰهُ ٱلنَّارُ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ
Amharic Translation - Africa Academy72. እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲህ ነው።» ያሉ በእርግጥ በአላህ ካዱ:: አል መሲህም አለ፡- «የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ብቻ ተገዙ:: እነሆ በአላህ የሚያጋራ ሰው ሁሉ አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ:: መኖሪያዉም እሳት ናት:: ለበዳዩችም ምንም ረዳቶች የሏቸዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَّقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ ثَالِثُ ثَلَٰثَةٍ وَمَا مِنْ إِلَٰهٍ إِلَّآ إِلَٰهٌ وَٰحِدٌ وَإِن لَّمْ يَنتَهُوا۟ عَمَّا يَقُولُونَ لَيَمَسَّنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy73. እነዚያ «አላህ የሶስት ሶስተኛ ነው።» ያሉ በእርግጥ ሁሉ ካዱ። ከአምላክም አንድ አምላክ ብቻ እንጂ ሌላ አምላክ የለም:: ከሚሉትም ነገር ካልተከለከሉ እነዚያን የካዱትን ሁሉ አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَلَا يَتُوبُونَ إِلَى ٱللَّهِ وَيَسْتَغْفِرُونَهُۥ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy74. ለመሆኑ እንደነዚህ አይነቶች ወደ አላህ አይመለሱምና ምህረትን አይለምኑትምን? አላህ መሀሪና አዛኝ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَّا ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ ٱلرُّسُلُ وَأُمُّهُۥ صِدِّيقَةٌ كَانَا يَأْكُلَانِ ٱلطَّعَامَ ٱنظُرْ كَيْفَ نُبَيِّنُ لَهُمُ ٱلْـَٔايَٰتِ ثُمَّ ٱنظُرْ أَنَّىٰ يُؤْفَكُونَ
Amharic Translation - Africa Academy75. የመርየም ልጅ አልመሲህ ከበፊቱ ብዙ መልዕክተኞች የቀደሙት መልዕክተኛ እንጂ ሌላ አይደለም:: እናቱም በጣም እውነተኛ አማኝ ናት:: ሁለቱም ምግብን የሚበሉ ነበሩ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አናቅጽን ለከሓዲያን እንዴት እንደምናብራራና ከዚያ እነርሱ ከእውነት እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ أَتَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَمْلِكُ لَكُمْ ضَرًّا وَلَا نَفْعًا وَٱللَّهُ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْعَلِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy76. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከአላህ ሌላ ለእናንተ መጉዳትንና መጥቀምን የማይችልን ትገዛላችሁን? አላህ እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነው።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ غَيْرَ ٱلْحَقِّ وَلَا تَتَّبِعُوٓا۟ أَهْوَآءَ قَوْمٍ قَدْ ضَلُّوا۟ مِن قَبْلُ وَأَضَلُّوا۟ كَثِيرًا وَضَلُّوا۟ عَن سَوَآءِ ٱلسَّبِيلِ
Amharic Translation - Africa Academy77. (መልዕክተኛች ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ከእውነት ውጭ ወሰንን አትለፉ:: ፊትም የተሳሳቱትንና ብዙዎቹን ህዝቦች ያሳሳቱትን ከቀጥተኛው መንገድም አሁን የተሳሳቱትን ህዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች (ስሜቶች) አትከተሉ።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لُعِنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنۢ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ عَلَىٰ لِسَانِ دَاوُۥدَ وَعِيسَى ٱبْنِ مَرْيَمَ ذَٰلِكَ بِمَا عَصَوا۟ وَّكَانُوا۟ يَعْتَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy78. ከኢስራኢል ልጆች መካከል እነዚያ በአላህ የካዱት በዳውድና በመርየም ልጅ ዒሳ አንደበት ተረገሙ:: ይህም የአላህን ትዕዛዝ በመጣሳቸውና ወሰን የሚያልፉ በመሆናቸው ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَانُوا۟ لَا يَتَنَاهَوْنَ عَن مُّنكَرٍ فَعَلُوهُ لَبِئْسَ مَا كَانُوا۟ يَفْعَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy79. ይሰሩት ከነበረው መጥፎ ነገር አይከላከሉም ነበር:: ይሰሩት የነበረው ነገር በእርግጥ ከፋ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تَرَىٰ كَثِيرًا مِّنْهُمْ يَتَوَلَّوْنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَبِئْسَ مَا قَدَّمَتْ لَهُمْ أَنفُسُهُمْ أَن سَخِطَ ٱللَّهُ عَلَيْهِمْ وَفِى ٱلْعَذَابِ هُمْ خَٰلِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ ብዙዎቹን ከእነዚያ ከካዱት ጋር ሲወዳጁ ታያለህ:: በእነርሱ ላይ አላህ በመቆጣቱ ለእነርሱ ነፍሶቻቸው ያስቀደሙት ስራ በጣም ከፋ። እነርሱም በቅጣቱ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ كَانُوا۟ يُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلنَّبِىِّ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيْهِ مَا ٱتَّخَذُوهُمْ أَوْلِيَآءَ وَلَٰكِنَّ كَثِيرًا مِّنْهُمْ فَٰسِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy81. በአላህና በነቢዩ ወደርሱም በተወረደው ቁርኣን የሚያምኑ በኾኑ ኖሮ ወዳጆች አድርገው ባልያዙዋቸው ነበር፡፡ ግን ከእነርሱ ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَتَجِدَنَّ أَشَدَّ ٱلنَّاسِ عَدَٰوَةً لِّلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱلْيَهُودَ وَٱلَّذِينَ أَشْرَكُوا۟ وَلَتَجِدَنَّ أَقْرَبَهُم مَّوَدَّةً لِّلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّا نَصَٰرَىٰ ذَٰلِكَ بِأَنَّ مِنْهُمْ قِسِّيسِينَ وَرُهْبَانًا وَأَنَّهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy82. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አይሁድና እነዚያ በአላህ ያጋሩት ለእነዚያ ላመኑት በጠላትነት ከሌሎች ሁሉ የበረቱ ሆነው ታገኛቸዋለህ:: ከእነርሱ መካከል እነዚያ «እኛ ክርስቲያኖች ነን።» ያሉትን ደግሞ ለእነዚያ ላመኑት በወዳጅነት ይበልጥ የቀረቧቸው ሆነው ታገኛቸዋለህ:: ይህም ከእነርሱ መካከል ቀሳውስትና መነኮሳት በመኖራቸውና እነርሱም የማይኮሩ በመሆናቸው ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا سَمِعُوا۟ مَآ أُنزِلَ إِلَى ٱلرَّسُولِ تَرَىٰٓ أَعْيُنَهُمْ تَفِيضُ مِنَ ٱلدَّمْعِ مِمَّا عَرَفُوا۟ مِنَ ٱلْحَقِّ يَقُولُونَ رَبَّنَآ ءَامَنَّا فَٱكْتُبْنَا مَعَ ٱلشَّٰهِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy83. ወደ መልዕክተኛው የተወረደውን ቁርኣን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከመረዳታቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን ሲያፈሱ ታያለህ:: ይላሉም: «ጌታችን ሆይ! ባንተ አምነናልና ከመስካሪዎች ጋር ፃፈን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا لَنَا لَا نُؤْمِنُ بِٱللَّهِ وَمَا جَآءَنَا مِنَ ٱلْحَقِّ وَنَطْمَعُ أَن يُدْخِلَنَا رَبُّنَا مَعَ ٱلْقَوْمِ ٱلصَّٰلِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy84. «ጌታችን ከመልካም ሰሪዎች ጋር ገነትን ሊያስገባን የምንከጅል ስንሆን በአላህና ከእርሱ በመጣልን እውነት ሁሉ የማናምንበት ምን ምክንያት አለን?» (ይላሉ።)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَثَٰبَهُمُ ٱللَّهُ بِمَا قَالُوا۟ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَذَٰلِكَ جَزَآءُ ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy85. እናም ባሉት ምክንያት አላህ በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶችን በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ መነዳቸው። ይህም የበጎ ሰሪዎች ዋጋ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَكَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَآ أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلْجَحِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy86. እነዚያም የካዱና በአናቅጻችን ያስተባበሉ ሁሉ የእሳት ጓዶች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تُحَرِّمُوا۟ طَيِّبَٰتِ مَآ أَحَلَّ ٱللَّهُ لَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلْمُعْتَدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy87. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ለእናንተ የፈቀደላችሁን ጣፋጮች በራሳችሁ ላይ እርም አታድርጉ:: ወሰንንም አትለፉ:: አላህ ወሰን አላፊዎችን ሁሉ አይወድምና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكُلُوا۟ مِمَّا رَزَقَكُمُ ٱللَّهُ حَلَٰلًا طَيِّبًا وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ٱلَّذِىٓ أَنتُم بِهِۦ مُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy88. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ የተፈቀደ ጥሩ ሲሆን ብሉ። ያንን ያመናችሁበት ጌታችሁን አላህንም ፍሩ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَا يُؤَاخِذُكُمُ ٱللَّهُ بِٱللَّغْوِ فِىٓ أَيْمَٰنِكُمْ وَلَٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا عَقَّدتُّمُ ٱلْأَيْمَٰنَ فَكَفَّٰرَتُهُۥٓ إِطْعَامُ عَشَرَةِ مَسَٰكِينَ مِنْ أَوْسَطِ مَا تُطْعِمُونَ أَهْلِيكُمْ أَوْ كِسْوَتُهُمْ أَوْ تَحْرِيرُ رَقَبَةٍ فَمَن لَّمْ يَجِدْ فَصِيَامُ ثَلَٰثَةِ أَيَّامٍ ذَٰلِكَ كَفَّٰرَةُ أَيْمَٰنِكُمْ إِذَا حَلَفْتُمْ وَٱحْفَظُوٓا۟ أَيْمَٰنَكُمْ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمْ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy89. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ከመሀሎቻችሁ መካከል በውድቁ አይዛችሁም:: ባሰባችሁበት መሀላ ግን ይይዛችኋል:: እናም መሀላዎችን ባፈረሳችሁ ጊዜ ማሰረዣው ቤተሰቦቻችሁን ከምትመግቡት ከመካከለኛው ምግብ ለአስር ሚስኪኖች ማብላት ወይም እነርሱን ማልበስ ወይም የአንዲትን ባሪያ ጫንቃን ነፃ ማውጣት ነው:: ከተባሉት አንዱንም ያለገኘ ሶስት ቀናትን መፆም ብቻ ነው:: ይህ በማላችሁና መሀላዎቻችሁን ባፈረሳችሁ ጊዜ ማሰረዣው ነው:: መሀላዎቻችሁንም ጠብቁ:: ልክ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ አናቅጽን ያብራራል:: እናንተም ልታመሰግኑት ይከጀላልና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّمَا ٱلْخَمْرُ وَٱلْمَيْسِرُ وَٱلْأَنصَابُ وَٱلْأَزْلَٰمُ رِجْسٌ مِّنْ عَمَلِ ٱلشَّيْطَٰنِ فَٱجْتَنِبُوهُ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy90. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ፤ የቁማር ጫዎታ፤ ጣዖታትን መገዛት እና አዝላምም ከሰይጣን ስራ የሆነ እና እርኩስ ተግባር ብቻ ናቸው። ትድኑ ዘንድም ራቁት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّمَا يُرِيدُ ٱلشَّيْطَٰنُ أَن يُوقِعَ بَيْنَكُمُ ٱلْعَدَٰوَةَ وَٱلْبَغْضَآءَ فِى ٱلْخَمْرِ وَٱلْمَيْسِرِ وَيَصُدَّكُمْ عَن ذِكْرِ ٱللَّهِ وَعَنِ ٱلصَّلَوٰةِ فَهَلْ أَنتُم مُّنتَهُونَ
Amharic Translation - Africa Academy91. ሰይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር አማካኝነት በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጭርና አላህን ከማውሳትና ከስግደት ሊያግዳችሁ ብቻ ነው:: ታዲያ እናንተ ከእነዚህ ነገሮች ተከልካዩች ናችሁን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُوا۟ ٱلرَّسُولَ وَٱحْذَرُوا۟ فَإِن تَوَلَّيْتُمْ فَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّمَا عَلَىٰ رَسُولِنَا ٱلْبَلَٰغُ ٱلْمُبِينُ
Amharic Translation - Africa Academy92. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህን ብቻ ታዘዙ:: መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: ተጠንቀቁ:: ብትሸሹም በመልዕክተኛችን ላይ ያለበት በግልጽ መልዕክቱን ማድረስ ብቻ መሆኑን እወቁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَيْسَ عَلَى ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ جُنَاحٌ فِيمَا طَعِمُوٓا۟ إِذَا مَا ٱتَّقَوا۟ وَّءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ ثُمَّ ٱتَّقَوا۟ وَّءَامَنُوا۟ ثُمَّ ٱتَّقَوا۟ وَّأَحْسَنُوا۟ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy93. በእነዚያ በአላህ ባመኑትና በጎ ስራዎችን በሰሩት ላይ ከተጠነቀቁና ካመኑ መልካምን ከሰሩ፤ ከዚያም ከተጠነቀቁና ካመኑ፤ ከዚያም ከተጠነቀቁና ስራንም ካሳመሩ ከመከልከሉ በፊት በተመገቡት ነገር ኃጢአት የለባቸዉም። አላህ ስራቸውን አሳማሪዎቹን ሁሉ ይወዳልና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَيَبْلُوَنَّكُمُ ٱللَّهُ بِشَىْءٍ مِّنَ ٱلصَّيْدِ تَنَالُهُۥٓ أَيْدِيكُمْ وَرِمَاحُكُمْ لِيَعْلَمَ ٱللَّهُ مَن يَخَافُهُۥ بِٱلْغَيْبِ فَمَنِ ٱعْتَدَىٰ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَلَهُۥ عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy94. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ በሐጅ ጊዜ እጆቻችሁና ጦሮቻችሁ (በሚያገኙት) በሚያድኑት ታዳኝ አውሬ አላህን በሩቁ ሆኖ የሚፈራውን ሰው ሊገልጽ ይሞክራችኋል:: ከዚያ በኋላ ወሰንን ያለፈና ያደነ ሰው ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለበት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَقْتُلُوا۟ ٱلصَّيْدَ وَأَنتُمْ حُرُمٌ وَمَن قَتَلَهُۥ مِنكُم مُّتَعَمِّدًا فَجَزَآءٌ مِّثْلُ مَا قَتَلَ مِنَ ٱلنَّعَمِ يَحْكُمُ بِهِۦ ذَوَا عَدْلٍ مِّنكُمْ هَدْيًۢا بَٰلِغَ ٱلْكَعْبَةِ أَوْ كَفَّٰرَةٌ طَعَامُ مَسَٰكِينَ أَوْ عَدْلُ ذَٰلِكَ صِيَامًا لِّيَذُوقَ وَبَالَ أَمْرِهِۦ عَفَا ٱللَّهُ عَمَّا سَلَفَ وَمَنْ عَادَ فَيَنتَقِمُ ٱللَّهُ مِنْهُ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ ذُو ٱنتِقَامٍ
Amharic Translation - Africa Academy95. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እናንተ በሐጅ ስራ ውስጥ ስትሆኑ አውሬን አትግደሉ:: ከናንተም እያወቀ አውሬን የገደለ ሰው ቅጣቱ ከናንተ መካከል ሁለት የፍትሀዊነት ባለቤቶች የሚፈርዱበትና ወደ ካዕባ ደራሽ መስዋዕት ሲሆን ከቤት እንሰሳዎች የገደለውን ነገር ብጤ መስጠት ወይም ሚስኪኖችን ማብላት ወይም የዚህን ልክ መፆም ማሰረዣው ነው:: ይህም የስራውን ከባድ ቅጣት እንዲቀምስ ነው:: ሳይከለከል በፊት ላለፈው ነገር አላህ ይቅርታ አደረገ:: ወደ ጥፋቱ የተመለሰን ሁሉ አላህ ይበቀለዋል:: አላህ አሸናፊና የብቀላ ባለቤት ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُحِلَّ لَكُمْ صَيْدُ ٱلْبَحْرِ وَطَعَامُهُۥ مَتَٰعًا لَّكُمْ وَلِلسَّيَّارَةِ وَحُرِّمَ عَلَيْكُمْ صَيْدُ ٱلْبَرِّ مَا دُمْتُمْ حُرُمًا وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ٱلَّذِىٓ إِلَيْهِ تُحْشَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy96. ሙስሊሞች ሆይ! የባህር እንሰሳና ምግቡ ለእናንተና ለመንገደኞች ሁሉ መጠቀሚያ ይሆን ዘንድ ተፈቀደላችሁ:: በሐጅ ላይ እስካላችሁ ድረስ ግን የየብስ አውሬ በእናንተ ላይ እርም ተደረገ:: ያንን ወደ እርሱ የምትሰበሰቡበትን አላህን ፍሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
جَعَلَ ٱللَّهُ ٱلْكَعْبَةَ ٱلْبَيْتَ ٱلْحَرَامَ قِيَٰمًا لِّلنَّاسِ وَٱلشَّهْرَ ٱلْحَرَامَ وَٱلْهَدْىَ وَٱلْقَلَٰٓئِدَ ذَٰلِكَ لِتَعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَأَنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy97. አላህ ያ የተከበረውን ቤት ካዕባን፤ ክልክል የሆነውን ወር፤ ወደ መካ የሚወስደውን መስዋዕቱንና ባለ ምልክቶቹን መንጋዎች ለሰዎች እምነት (ዋልታ) መቋቋሚያ አደረገ:: ይህ የሆነው አላህ በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑንና ሁሉን ነገር አዋቂ መሆኑን እንድታውቁ ዘንድ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ وَأَنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy98. (ሰዎች ሆይ!) አላህ ቅጣተ ብርቱም መሀሪና አዛኝም መሆኑን እወቁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَّا عَلَى ٱلرَّسُولِ إِلَّا ٱلْبَلَٰغُ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ مَا تُبْدُونَ وَمَا تَكْتُمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy99. በመልዕክተኛው ላይ መልዕክቱን ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትም:: አላህ የምትገልጹትንም ሆነ የምትደብቁትን ሁሉ ያውቃል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُل لَّا يَسْتَوِى ٱلْخَبِيثُ وَٱلطَّيِّبُ وَلَوْ أَعْجَبَكَ كَثْرَةُ ٱلْخَبِيثِ فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ يَٰٓأُو۟لِى ٱلْأَلْبَٰبِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy100. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመጥፎው ነገር ብዛቱ ቢያስገርምህ እንኳ መጥፎና ጥሩው መቼም አይስተካከሉም። ባለ ልቦች ሆይ! ትድኑ ዘንድ አላህን ብቻ ፍሩ።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَسْـَٔلُوا۟ عَنْ أَشْيَآءَ إِن تُبْدَ لَكُمْ تَسُؤْكُمْ وَإِن تَسْـَٔلُوا۟ عَنْهَا حِينَ يُنَزَّلُ ٱلْقُرْءَانُ تُبْدَ لَكُمْ عَفَا ٱللَّهُ عَنْهَا وَٱللَّهُ غَفُورٌ حَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy101. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ ቢገለጹ ከሚያስከፏችሁ ነገሮች አትጠይቁ:: ቁርኣንም በሚወርድበት ጊዜ ከእርሷ ብትጠይቁ ለእናንተ ትገለፃለች:: ከእርሷ ግን አላህ ይቅርታ አደረገ:: አላህ መሀሪና ታጋሽ ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَدْ سَأَلَهَا قَوْمٌ مِّن قَبْلِكُمْ ثُمَّ أَصْبَحُوا۟ بِهَا كَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy102. ከናንተ በፊት የነበሩ ሕዝቦች ተመሳሳዩን ጠየቁ። ከዚያም (በትክክል ባለመፈጸማቸው ምክንያት) ከካሐዲያን ሆኑ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا جَعَلَ ٱللَّهُ مِنۢ بَحِيرَةٍ وَلَا سَآئِبَةٍ وَلَا وَصِيلَةٍ وَلَا حَامٍ وَلَٰكِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ يَفْتَرُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلْكَذِبَ وَأَكْثَرُهُمْ لَا يَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy103. አላህ «በሒራ»፤ «ሳኢባ»፤ «ወሲላ»ና «ሐም» የተባሉ ነገሮች ከሸሪዓ አላደረገም:: ግን እነዚያ የካዱት ህዝቦች በአላህ ላይ ውሸትን ይቀጥፋሉ:: አብዛሀኞቻቸውም አያስተውሉም። (1)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا۟ إِلَىٰ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ وَإِلَى ٱلرَّسُولِ قَالُوا۟ حَسْبُنَا مَا وَجَدْنَا عَلَيْهِ ءَابَآءَنَآ أَوَلَوْ كَانَ ءَابَآؤُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ شَيْـًٔا وَلَا يَهْتَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy104. «አላህ ወደ አወረደውና ወደ መልዕክተኛው ኑ» በተባሉ ጊዜ «አባቶቻችንን ያገኝንበት መንገድ ይበቃናል።» ይላሉ:: አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና ወደ ቀናው መንገድ የማይመሩ ቢሆኑም ይበቃቸዋልን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ عَلَيْكُمْ أَنفُسَكُمْ لَا يَضُرُّكُم مَّن ضَلَّ إِذَا ٱهْتَدَيْتُمْ إِلَى ٱللَّهِ مَرْجِعُكُمْ جَمِيعًا فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy105. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁን (ማዳን ኃላፊነቱ) በራሳችሁ ላይ ነው። ራሳችሁን ወደቀናው መንገድ ከመራችሁ የሌሎች መሳሳት እናንተን አይጎዳችሁም:: የሁላችሁም መመለሻ ወደ አላህ ነው። እናም ትሰሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ شَهَٰدَةُ بَيْنِكُمْ إِذَا حَضَرَ أَحَدَكُمُ ٱلْمَوْتُ حِينَ ٱلْوَصِيَّةِ ٱثْنَانِ ذَوَا عَدْلٍ مِّنكُمْ أَوْ ءَاخَرَانِ مِنْ غَيْرِكُمْ إِنْ أَنتُمْ ضَرَبْتُمْ فِى ٱلْأَرْضِ فَأَصَٰبَتْكُم مُّصِيبَةُ ٱلْمَوْتِ تَحْبِسُونَهُمَا مِنۢ بَعْدِ ٱلصَّلَوٰةِ فَيُقْسِمَانِ بِٱللَّهِ إِنِ ٱرْتَبْتُمْ لَا نَشْتَرِى بِهِۦ ثَمَنًا وَلَوْ كَانَ ذَا قُرْبَىٰ وَلَا نَكْتُمُ شَهَٰدَةَ ٱللَّهِ إِنَّآ إِذًا لَّمِنَ ٱلْـَٔاثِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy106. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አንዳችሁ ሞት በመጣበት ጊዜ በኑዛዜ ወቅት በመካከላችሁ ለምስክርነት ከናንተ መካከል ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶች የሆኑ ሰዎች፤ ወይም በምድር ብትጓዙና የሞት አደጋ ብትነካችሁ ከሌሎቻችሁ የሆኑ ሁለት ሌሎች ሰዎች መመስከር ነው:: ብትጠራጠሩም ከአስር ሶላት በኋላ አቁሟቸውና «የሚመሰክርለት ሰው የዝምድና ባለቤት ቢሆንም እንኳን በእርሱ ዋጋን አንገዛም:: የአላህን ምስክርነት አንደብቅም:: ያን ጊዜማ ደብቀን ብንገኝ ከኃጢአተኞች ነን።» ብለው በአላህ ስም ይምላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِنْ عُثِرَ عَلَىٰٓ أَنَّهُمَا ٱسْتَحَقَّآ إِثْمًا فَـَٔاخَرَانِ يَقُومَانِ مَقَامَهُمَا مِنَ ٱلَّذِينَ ٱسْتَحَقَّ عَلَيْهِمُ ٱلْأَوْلَيَٰنِ فَيُقْسِمَانِ بِٱللَّهِ لَشَهَٰدَتُنَآ أَحَقُّ مِن شَهَٰدَتِهِمَا وَمَا ٱعْتَدَيْنَآ إِنَّآ إِذًا لَّمِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy107. ሆኖም እነርሱ ኃጢአት (በውሸት ምስክርነት) የተገቡ መሆናቸው ቢታወቅ ከእነዚያ ከሟቹ ቅርብ ዘመዶች ውርስ ከተገባቸው ሁለት ሌሎች ሰዎች በስፍራቸው በምስክሮች ስፍራ ይቆሙና «ምስክርነታችን ከእነርሱ ምስክርነት ይልቅ እውነት ነው ወሰንም አላለፍንም። ያን ጊዜ እኛ ከበዳዩቹ ነን።» ሲሉ በአላህ ይምላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَٰلِكَ أَدْنَىٰٓ أَن يَأْتُوا۟ بِٱلشَّهَٰدَةِ عَلَىٰ وَجْهِهَآ أَوْ يَخَافُوٓا۟ أَن تُرَدَّ أَيْمَٰنٌۢ بَعْدَ أَيْمَٰنِهِمْ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَٱسْمَعُوا۟ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلْفَٰسِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy108. ይህ (አሰራር) ምስክርነት በተገቢው ላይ ለማምጣታቸው ወይም ከመሀላዎቻቸው በኋላ የመሀላዎቹ ወደ ወራሾች መመለስን ለመፍራት በጣም የቀረበ ነው:: አላህን ብቻ ፍሩ:: እሱን ብቻ ስሙትም:: አላህ አመጸኛ ሕዝቦችን አይመራምና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ يَجْمَعُ ٱللَّهُ ٱلرُّسُلَ فَيَقُولُ مَاذَآ أُجِبْتُمْ قَالُوا۟ لَا عِلْمَ لَنَآ إِنَّكَ أَنتَ عَلَّٰمُ ٱلْغُيُوبِ
Amharic Translation - Africa Academy109. (መልዕክተኛችን ሆይ!) አላህ መልዕክተኞቹን ሰብስቦ እንዲህ ባለ ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ፡- «ሕዝቦቻችሁ ምን መለሱላችሁ?» መልዕክተኞቹም: «እኛ እውቀቱ የለንም:: ሩቅ ሚስጥሮችን ሁሉ የምታውቀው አንተው ነህ።» ይላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَى ٱبْنَ مَرْيَمَ ٱذْكُرْ نِعْمَتِى عَلَيْكَ وَعَلَىٰ وَٰلِدَتِكَ إِذْ أَيَّدتُّكَ بِرُوحِ ٱلْقُدُسِ تُكَلِّمُ ٱلنَّاسَ فِى ٱلْمَهْدِ وَكَهْلًا وَإِذْ عَلَّمْتُكَ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَٱلتَّوْرَىٰةَ وَٱلْإِنجِيلَ وَإِذْ تَخْلُقُ مِنَ ٱلطِّينِ كَهَيْـَٔةِ ٱلطَّيْرِ بِإِذْنِى فَتَنفُخُ فِيهَا فَتَكُونُ طَيْرًۢا بِإِذْنِى وَتُبْرِئُ ٱلْأَكْمَهَ وَٱلْأَبْرَصَ بِإِذْنِى وَإِذْ تُخْرِجُ ٱلْمَوْتَىٰ بِإِذْنِى وَإِذْ كَفَفْتُ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ عَنكَ إِذْ جِئْتَهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْهُمْ إِنْ هَٰذَآ إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy110. አላህ እንዲህ በሚልበት ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ላንተና ለእናትህ የዋልኩላችሁን ውለታ አስታውስ:: በሩሀል ቁዱስ (በጅብሪል) አጠነከርኩህ:: በሕጻንነትህም አድገህም ሰዎችን ማናገር ቻልክ። መጽሐፉንና ጥበብን ተውራትንና ኢንጂልንም አስተማርኩህ:: ከጭቃም የወፍ ቅርጽ ዓይነት በፈቃዴ መሥራት ቻልክ:: በሷ ውስጥ ነፈህ:: በፈቃዴም እውነተኛ በራሪ ሆነች:: እውር ሆኖ የተወለደንና ለምጻምን በፈቃዴ መፈወስ ቻልክ:: ሟችንም በፈቃዴ አስነሳህ:: የኢስራኢልንም ልጆች ግልጽ መረጃ ባመጣህላቸው ጊዜ ሊያጠቁህ ሲያስቡ አቀብኩልህ:: ከመካከላቸዉም እነዚያ በአላህ የካዱት ‹ይህ ግልጽ ድግምት ነው› አሉ:: ይህን ሁሉ ውለታዬን አስታውስ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى ٱلْحَوَارِيِّـۧنَ أَنْ ءَامِنُوا۟ بِى وَبِرَسُولِى قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا وَٱشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy111. «ለሃዋሪያቱም፡- ‹በእኔና በመልዕክተኛዬ እመኑ።› የሚል ራዕይ በገለጽኩ ጊዜም የሆነውን አስታውስ። ‹አምነናል:: እኛ ሙስሊሞች ለመሆናችን ምስክር ሁን› አሉም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ قَالَ ٱلْحَوَارِيُّونَ يَٰعِيسَى ٱبْنَ مَرْيَمَ هَلْ يَسْتَطِيعُ رَبُّكَ أَن يُنَزِّلَ عَلَيْنَا مَآئِدَةً مِّنَ ٱلسَّمَآءِ قَالَ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy112. «ሃዋሪያቶቹም፡- ‹የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ጌታህ ከሰማይ ማዕድ ሊያወርድልን ይቻላልን?› ባሉ ጊዜ የሆነውን አስታውስ። ዒሳም፡-‹ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ አላህን ብቻ ፍሩ።› አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ نُرِيدُ أَن نَّأْكُلَ مِنْهَا وَتَطْمَئِنَّ قُلُوبُنَا وَنَعْلَمَ أَن قَدْ صَدَقْتَنَا وَنَكُونَ عَلَيْهَا مِنَ ٱلشَّٰهِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy113. «‹ከእርሱ ልንመገብ ልቦቻችንም እርካታን ይጎናጸፉ ዘንድ ብቻ ነው ይህን የጠየቅነው:: የነገርከንም ተጨባጭ እውነት መሆኑን ልናውቅና ለዚህም መስካሪዎች ለመሆን ፈልገን ነው።› አሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ ٱللَّهُمَّ رَبَّنَآ أَنزِلْ عَلَيْنَا مَآئِدَةً مِّنَ ٱلسَّمَآءِ تَكُونُ لَنَا عِيدًا لِّأَوَّلِنَا وَءَاخِرِنَا وَءَايَةً مِّنكَ وَٱرْزُقْنَا وَأَنتَ خَيْرُ ٱلرَّٰزِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy114. «የመርየም ልጅ ዒሳም፡- ‹ጌታችን አላህ ሆይ! ከሰማይ ማዕድን አውርድልን ለእኛ ለመጀመሪያዎቻችንና ለመጭዎቹም ትውልዶች በዓል (የደስታ እለት) ካንተ የሆነችም ተዐምር ትሆንልን ዘንድ :: ሲሳይንም ለግሰን:: አንተ ከለጋሾች ሁሉ የበለጥክ ለጋሽ ነህና› አለ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ ٱللَّهُ إِنِّى مُنَزِّلُهَا عَلَيْكُمْ فَمَن يَكْفُرْ بَعْدُ مِنكُمْ فَإِنِّىٓ أُعَذِّبُهُۥ عَذَابًا لَّآ أُعَذِّبُهُۥٓ أَحَدًا مِّنَ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy115. አላህም፡- «ማዕዷን አወርድላችኋለሁ:: ግና ከዚህ ተአምር በኋላ ከመካከላችሁ በእኔ ለካዱት ሁሉ በዓለማት ላይ ማንንም የማልቀጣውን አስከፊ ቅጣት እቀጣቸዋለሁ።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَى ٱبْنَ مَرْيَمَ ءَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ ٱتَّخِذُونِى وَأُمِّىَ إِلَٰهَيْنِ مِن دُونِ ٱللَّهِ قَالَ سُبْحَٰنَكَ مَا يَكُونُ لِىٓ أَنْ أَقُولَ مَا لَيْسَ لِى بِحَقٍّ إِن كُنتُ قُلْتُهُۥ فَقَدْ عَلِمْتَهُۥ تَعْلَمُ مَا فِى نَفْسِى وَلَآ أَعْلَمُ مَا فِى نَفْسِكَ إِنَّكَ أَنتَ عَلَّٰمُ ٱلْغُيُوبِ
Amharic Translation - Africa Academy116. (መልዕክተኛች ሙሐመድ ሆይ!) አላህ፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ሰዎችን ‹እኔንና እናቴን ከአላህ ውጭ ሁለት አማልዕክት አድርጋችሁ ያዙን።› ብለሃልን?» በሚለው ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ:: ዒሳም አለ፡- «ክብርና ልዕልና ላንተ ብቻ ይሁን! ለእኔ ልለው የማይገባኝን ነገር ማለቴ ፈጽሞ አግባብ አይደለም:: ይህን ተናግሬ ከሆነም ታውቀዋለህ:: አንተ በውስጤ ያለውን ሁሉ ጠንቅቀህ ታውቃለህ:: እኔ ግን ባንተ ውስጥ ያለውን አላውቅም:: አንተ ሩቅ ሚስጥራትን ሁሉ አዋቂ ነህና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ وَكُنتُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًا مَّا دُمْتُ فِيهِمْ فَلَمَّا تَوَفَّيْتَنِى كُنتَ أَنتَ ٱلرَّقِيبَ عَلَيْهِمْ وَأَنتَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ شَهِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy117. «የነገርኳቸው ያን ያዘዝከኝን ብቻ ነው:: ‹የእኔም የእናንተም ጌታ የሆነውን አላህን ብቻ አምልኩ ነው› ያልኳቸው:: በመካከላቸው በነበርኩበት ወቅት ስለ እነርሱ መስካሪ ነበርኩ:: እንዳርግ ካደረግከኝ በኋላ ግን የእነርሱ ጠባቂና ተቆጣጣሪ አንተው ብቻ ነበርክ:: አንተ በሁሉም ነገር ላይ መስካሪ ነህና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِن تُعَذِّبْهُمْ فَإِنَّهُمْ عِبَادُكَ وَإِن تَغْفِرْ لَهُمْ فَإِنَّكَ أَنتَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy118. «ብትቀጣቸው እነርሱ የአንተው ባሮችህ ናቸው:: ብትምራቸው ደግሞ አንተ ኃያልና ጥበበኛ ነህ።» ይላል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ ٱللَّهُ هَٰذَا يَوْمُ يَنفَعُ ٱلصَّٰدِقِينَ صِدْقُهُمْ لَهُمْ جَنَّٰتٌ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًا رَّضِىَ ٱللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا۟ عَنْهُ ذَٰلِكَ ٱلْفَوْزُ ٱلْعَظِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy119. አላህም እንዲህ ይላል፡- «ይህ ቀን እውነቱ ለእውነተኞች የሚጠቅምበት ቀን ነው::» ለእውነተኞች ከስሮቿ ወንዞች የሚፈሱባት ገነት ተዘጋጅቶላቸዋል:: በውስጧም ለዝንተ ዓለም ይኖራሉ:: አላህ በእነርሱ ተግባር ተደስቷል:: እነርሱም በእርሱ ችሮታ ተደስተዋል:: ይህ ታላቅ ስኬት ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِلَّهِ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا فِيهِنَّ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌۢ
Amharic Translation - Africa Academy120. የሰማያት የምድርና በውስጣቸው ያሉ ፍጡራን ሁሉ ባለቤትነት የአላህ ብቻ ነው:: እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→