caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Nisaa፣ አንቀጽ 162

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 92 · 4:162

لَّٰكِنِ ٱلرَّٰسِخُونَ فِى ٱلْعِلْمِ مِنْهُمْ وَٱلْمُؤْمِنُونَ يُؤْمِنُونَ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيْكَ وَمَآ أُنزِلَ مِن قَبْلِكَ وَٱلْمُقِيمِينَ ٱلصَّلَوٰةَ وَٱلْمُؤْتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَٱلْمُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ أُو۟لَٰٓئِكَ سَنُؤْتِيهِمْ أَجْرًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy162. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ግን ከእነርሱ ውስጥ በእውቀት የጠለቁት ክፍሎችና ትክክለኛ ምዕመናኖቹ ባንተ ላይ በተወረደውና ካንተ በፊት በተወረደው መጽሐፍ ያምናሉ። ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው ሰጋጆቹ፣ ዘካንም ሰጪዎቹ በአላህና በመጨረሻው ቀንም ትክክለኛ አማኞቹን እነዚያ ታላቅ ምንዳን በእርግጥ እንሰጣቸዋለን::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqግን ከነርሱ ውስጥ በዕውቀት የጠለቁትና ምእምናኖቹ በአንተ ላይ በተወረደውና ከአንተም በፊት በተወረደው መጽሐፍ የሚያምኑ ሲኾኑ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው ሰጋጆችን ዘካንም ሰጪዎቹ በአላህና በመጨረሻዎቹም ቀን አማኞቹ እነዚያ ታላቅ ምንዳን በእርግጥ እንሰጣቸዋለን፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70