caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Nisaa፣ አንቀጽ 157

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 92 · 4:157

وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا ٱلْمَسِيحَ عِيسَى ٱبْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ ٱللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ ٱخْتَلَفُوا۟ فِيهِ لَفِى شَكٍّ مِّنْهُ مَا لَهُم بِهِۦ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا ٱتِّبَاعَ ٱلظَّنِّ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًۢا

Amharic Translation - Africa Academy157. «እኛ የአላህ መልዕክተኛ የመርየም ልጅ አል መሲህ ዒሳን ገደልን።» በማለታቸውም ረገምናቸው:: አልገደሉትም:: አልሰቀሉትምም:: ግን የተገደለው ሰው ለእነርሱ በዒሳ ተመሰለባቸው:: እነዚያ በእርሱ ጉዳይ የተለያዩት በእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም እርግጠኛ እውቀት የላቸዉም:: በእርግጥም አልገደሉትም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70