وَمَن يُشَاقِقِ ٱلرَّسُولَ مِنۢ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ ٱلْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ ٱلْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِۦ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِۦ جَهَنَّمَ وَسَآءَتْ مَصِيرًا
Amharic Translation - Africa Academy115. ቅኑ መንገድ ለእርሱ ከተገለጸት በኋላ መልዕክተኛውን የሚቃረንና ከምዕመናኖቹ መንገድ ሌላ የሆነን የሚከተል ሁሉ በመረጠው ጥመት ላይ እንተወዋለን። ወደ ገሀነምም እናስገባዋለን:: መመለሻይቱም ገሀነም ከፋች።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናገባዋለን፡፡ መመለሻይቱም ከፋች!