أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ قِيلَ لَهُمْ كُفُّوٓا۟ أَيْدِيَكُمْ وَأَقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُوا۟ ٱلزَّكَوٰةَ فَلَمَّا كُتِبَ عَلَيْهِمُ ٱلْقِتَالُ إِذَا فَرِيقٌ مِّنْهُمْ يَخْشَوْنَ ٱلنَّاسَ كَخَشْيَةِ ٱللَّهِ أَوْ أَشَدَّ خَشْيَةً وَقَالُوا۟ رَبَّنَا لِمَ كَتَبْتَ عَلَيْنَا ٱلْقِتَالَ لَوْلَآ أَخَّرْتَنَآ إِلَىٰٓ أَجَلٍ قَرِيبٍ قُلْ مَتَٰعُ ٱلدُّنْيَا قَلِيلٌ وَٱلْـَٔاخِرَةُ خَيْرٌ لِّمَنِ ٱتَّقَىٰ وَلَا تُظْلَمُونَ فَتِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ለእነርሱ፡- «እጆቻችሁን ከመጋደል ሰብስቡ፤ ሶላትን ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፤ ግዴታ ምጽዋትን ስጡ።» ወደ ተባሉት አላየህምን? በእነርሱ ላይ መጋደል ግዴታ በሆነባቸው ጊዜ ደግሞ ከእነርሱ መካከል ከፊሎቹ ወዲያውኑ ሰዎችን ልክ አላህን እንደሚፈሩ ወይም የበለጠ ይፈራሉ:: «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ መጋደልን ለምን ደነገግህ? እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አታቆየንም ኖሯልን?» ይላሉ:: «የቅርቢቱ ሕይወት ጥቅም አነስተኛ ነው:: የመጨረሻይቱ ዓለም ጥቅም ግን አላህን ለሚፈራ ሁሉ በላጭ ነው። በተምር ፍሬ ውስጥ ያለችን ክር መሰል ያህል እንኳ አትበደሉም።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወደእነዚያ ለእነርሱ፡- እጆቻችሁን (ከመጋደል) ሰብስቡ፣ ሶላትንም ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፣ ግዴታ ምጽዋትም ስጡ ወደ ተባሉት አላየህምን በእነርሱም ላይ መጋደል በተጻፈ ጊዜ ከእነሱ ከፊሎቹ ወዲያውኑ ሰዎችን አላህን እንደሚፈሩ ወይም የበለጠ ፍራቻን ይፈራሉ፡፡ «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ መጋደልን ለምን ደነገግክ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አታቆየንም ኖሮአልን» ይላሉም፡፡ «የቅርቢቱ ሕይወት ጥቅም አነስተኛ ነው፡፡ መጨረሻይቱም ዓለም አላህን ለሚፈራ ሰው በላጭ ናት፡፡ በተምር ፍሬ ውስጥ ያለን ክር ያህል እንኳ አትበደሉም» በላቸው፡፡