يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌ مِّنْهُ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًا لَّكُمْ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌ وَٰحِدٌ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy171. እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ:: በአላህም ላይ እውነትን እንጂ አትናገሩ:: የመርየም ልጅ አል መሲህ ዒሳ የአላህ መልዕክተኛ ወደ መርየም የጣላት የሁን ቃሉና ከእርሱ የሆነ መንፈስ ብቻ ነው:: በአላህና በመላዕክተኞቹ እመኑ:: «አማልዕክት ሶስት ናቸው።» አትበሉ:: ተከልከሉ:: ለእናንተ የተሻለ ይሆናልና:: አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: ለእርሱም ልጅ ያለው ከመሆን የጠራ ነው:: በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: መመኪያነትም በአላህ በቃ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ የአላህ መልክተኛ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃሉም ከእርሱ የኾነ መንፈስም ብቻ ነው፡፡ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ፡፡ « (አማልክት) ሦስት ናቸው» አትበሉም፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ ልጅ ያለው ከመኾን የጠራ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ የርሱ ነው፡፡ መመኪያም በአላህ በቃ፡፡