مِّنَ ٱلَّذِينَ هَادُوا۟ يُحَرِّفُونَ ٱلْكَلِمَ عَن مَّوَاضِعِهِۦ وَيَقُولُونَ سَمِعْنَا وَعَصَيْنَا وَٱسْمَعْ غَيْرَ مُسْمَعٍ وَرَٰعِنَا لَيًّۢا بِأَلْسِنَتِهِمْ وَطَعْنًا فِى ٱلدِّينِ وَلَوْ أَنَّهُمْ قَالُوا۟ سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا وَٱسْمَعْ وَٱنظُرْنَا لَكَانَ خَيْرًا لَّهُمْ وَأَقْوَمَ وَلَٰكِن لَّعَنَهُمُ ٱللَّهُ بِكُفْرِهِمْ فَلَا يُؤْمِنُونَ إِلَّا قَلِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy46. ከእነዚያ ከአይሁዳውያን መካከል ንግግሮችን ከስፍራዎቹ የሚያጣምሙ አሉ። «ንግግርክን ሰማንና ትእዛዝክን አመጽን፤ የማትሰማም ስትሆን እስቲ ስማ።» ይላሉ:: በምላሶቻቸዉም ለማጣመምና ሃይማኖትንም ለመዝለፍ በማሰብ "ራዒና" ይላሉ:: እነርሱም «ሰማንና ታዘዝን፤ ስማን ተመልከተንም።» ባሉ ኖሮ ለእነርሱም መልካምና ትክክለኛ በሆነ ነበር:: ግን በክህደታቸው ምክንያት አላህ ረገማቸው:: ከእነርሱም መካከል ጥቂቶች እንጂ አያምኑም።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከነዚያ አይሁዳውያን ከኾኑት ሰዎች ንግግሮችን ከስፍራዎቹ የሚያጣምሙ አልሉ፡፡ «ሰማንም አመጽንም የማትሰማም ስትኾን ስማ» ይላሉ፡፡ በምላሶቻቸውም ለማጣመምና ሃይማኖትንም ለመዝለፍ ራዒና ይላሉ፡፡ እነሱም «ሰማን ታዘዝንም ስማም ተመልከተንም» ባሉ ኖሮ ለነሱ መልካምና ትክክለኛ በኾነ ነበር፡፡ ግን በክህደታቸው አላህ ረገማቸው፡፡ ጥቂትንም እንጅ አያምኑም፡፡