إِلَّا ٱلَّذِينَ يَصِلُونَ إِلَىٰ قَوْمٍۭ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَهُم مِّيثَٰقٌ أَوْ جَآءُوكُمْ حَصِرَتْ صُدُورُهُمْ أَن يُقَٰتِلُوكُمْ أَوْ يُقَٰتِلُوا۟ قَوْمَهُمْ وَلَوْ شَآءَ ٱللَّهُ لَسَلَّطَهُمْ عَلَيْكُمْ فَلَقَٰتَلُوكُمْ فَإِنِ ٱعْتَزَلُوكُمْ فَلَمْ يُقَٰتِلُوكُمْ وَأَلْقَوْا۟ إِلَيْكُمُ ٱلسَّلَمَ فَمَا جَعَلَ ٱللَّهُ لَكُمْ عَلَيْهِمْ سَبِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy90. እነዚያ በእናተና በእነርሱ መካከል ቃል ኪዳን ወዳላቸው ህዝቦች የሚጠጉ፤ ወይም እናንተን ለመጋደልም ይሁን ወገኖቻቸውን ለመጋደል ልቦቻቸው የተጨነቁ ሆነው ወደ እናንተ የመጡ ሲቀሩ እነዚያንማ አትጋደሏቸው:: አላህ በፈለገ ኖሮ በእናንተ ላይ ሀይል በሰጣቸውና በተዋጓችሁ ነበር:: ቢተዋችሁ ባይዋጓችሁ ወደ እናንተ የእርቅን ሀሳብ ቢያቀርቡ አላህ ለእናንተ በእነርሱ ላይ የመዋጋት መንገድን አላደረገም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያ በእናንተና በእነርሱ መካከል ቃል ኪዳን ወዳላቸው ሕዝቦች የሚጠጉና ወይም እናንተን ለመጋደል ወይም ወገኖቻቸውን ለመጋደል ልቦቻቸው የተጨነቁ ኾነው የመጧዋችሁ ሲቀሩ፤ (እነዚያንስ አትጋደሉዋቸው)፡፡ አላህም በሻ ኖሮ በእናንተ ላይ ኀይል በሰጣቸውና በተጋደሉዋችሁ ነበር፡፡ ቢተዋችሁና ባይጋደሉዋችሁም ወደ እናንተም እርቅን ቢያቀርቡ አላህ ለእናንተ በነሱ ላይ (የመጋደል) መንገድን አላደረገም፡፡