caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Nisaa፣ አንቀጽ 81

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 92 · 4:81

وَيَقُولُونَ طَاعَةٌ فَإِذَا بَرَزُوا۟ مِنْ عِندِكَ بَيَّتَ طَآئِفَةٌ مِّنْهُمْ غَيْرَ ٱلَّذِى تَقُولُ وَٱللَّهُ يَكْتُبُ مَا يُبَيِّتُونَ فَأَعْرِضْ عَنْهُمْ وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy81. አጠገብህ ሲሆኑ የአንተ ታዛዥ ነን ይላሉ:: ካንተ ዘንድ በወጡ ጊዜ ከእነርሱ ከፊሎቹ ከዚያ በአጠገብህ ከሚሉት ሌላን በልቦቻቸው ያሳድራሉ:: አላህ በልቦቻቸው የሚያሳድሩትን ነገር ሁሉ ይጽፋል:: ስለዚህ ተዋቸውና በአላህ ላይ ብቻ ተመካ:: መመኪያነት አላህ ብቻ በቃ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«(ነገራችን) መታዘዝ ነው» ይላሉም፤ ከአንተም ዘንድ በወጡ ጊዜ ከነርሱ ከፊሎቹ ከዚያ (በፊትህ) ከሚሉት ሌላን (በልቦቻቸው) ያሳድራሉ፡፡ አላህም የሚያሳድሩትን ነገር ይጽፋል፡፡ ስለዚህ ተዋቸው፡፡ በአላህም ላይ ተጠጋ፡፡ መጠጊያም በአላህ በቃ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70