وَإِذَا جَآءَهُمْ أَمْرٌ مِّنَ ٱلْأَمْنِ أَوِ ٱلْخَوْفِ أَذَاعُوا۟ بِهِۦ وَلَوْ رَدُّوهُ إِلَى ٱلرَّسُولِ وَإِلَىٰٓ أُو۟لِى ٱلْأَمْرِ مِنْهُمْ لَعَلِمَهُ ٱلَّذِينَ يَسْتَنۢبِطُونَهُۥ مِنْهُمْ وَلَوْلَا فَضْلُ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَتُهُۥ لَٱتَّبَعْتُمُ ٱلشَّيْطَٰنَ إِلَّا قَلِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy83. ሰላምን ወይም ስጋትን የሚመለከት ወሬ በመጣላቸው ጊዜ እርሱን ያሰራጫሉ (ያጋንናሉ)። ወደ መልዕክተኛውና ከእነርሱ መካከል የጉዳይ ባለቤቶች ወደ ሆኑት አዋቂዎቹ በመለሱት ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ መካከል ነገሩን በትክክል የሚረዱት ክፍሎች ባወቁት ነበር:: በእናንተ ላይ የአላህን ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከጥቂቶቹ በስተቀር ሰይጣንን በተከተላችሁ ነበር።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከጸጥታ ወይም ከፍርሃት አንዳች (ወሬ) በመጣላቸውም ጊዜ እርሱን ያጋንናሉ፡፡ ወደ መልክተኛውና ከእነርሱ ወደ ትዕዛዙ ባለቤቶች (ወደ ዐዋቂዎቹ) በመለሱት ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ (ነገሩን) የሚያውጣጡት ባወቁት ነበር፡፡ በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከጥቂቶች በስተቀር ሰይጣንን በተከተላችሁ ነበር፡፡