caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Nisaa፣ አንቀጽ 78

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 92 · 4:78

أَيْنَمَا تَكُونُوا۟ يُدْرِككُّمُ ٱلْمَوْتُ وَلَوْ كُنتُمْ فِى بُرُوجٍ مُّشَيَّدَةٍ وَإِن تُصِبْهُمْ حَسَنَةٌ يَقُولُوا۟ هَٰذِهِۦ مِنْ عِندِ ٱللَّهِ وَإِن تُصِبْهُمْ سَيِّئَةٌ يَقُولُوا۟ هَٰذِهِۦ مِنْ عِندِكَ قُلْ كُلٌّ مِّنْ عِندِ ٱللَّهِ فَمَالِ هَٰٓؤُلَآءِ ٱلْقَوْمِ لَا يَكَادُونَ يَفْقَهُونَ حَدِيثًا

Amharic Translation - Africa Academy78. የትም ስፍራ ብትሆኑ ሞት ያገኛችኋል:: በጠነከሩ ህንፃዎች ውስጥም ብትደብቁ እንኳን:: ደግ ነገር ካገኛቸው «ይህ ከአላህ ዘንድ የመጣ ነው።» ይላሉ:: መከራ ካገኛቸው ግን «ይህ ካንተ ዘንድ የመጣ ነው።» ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሁሉም (ደጉም ክፉዉም) ከአላህ ዘንድ የመጣ ነው።» በላቸው:: እነዚህ ሰዎች ንግግርን ሊረዱ የማይቀርቡት ለምንድን ነው?
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«የትም ስፍራ ብትኾኑ በጠነከሩ ሕንጻዎች ውስጥ ብትኾኑም እንኳ ሞት ያገኛችኋል፡፡ ደግም ነገር ብታገኛቸው ይህች ከአላህ ዘንድ ናት» ይላሉ፡፡ መከራም ብታገኛቸው «ይህቺ ከአንተ ዘንድ ናት» ይላሉ፡፡ «ሁሉም (ደጉም ክፉውም) ከአላህ ዘንድ ነው» በላቸው፡፡ ለእነዚህም ሰዎች ንግግርን ሊረዱ የማይቀርቡት ምን አላቸው
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70