وَمَن لَّمْ يَسْتَطِعْ مِنكُمْ طَوْلًا أَن يَنكِحَ ٱلْمُحْصَنَٰتِ ٱلْمُؤْمِنَٰتِ فَمِن مَّا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُكُم مِّن فَتَيَٰتِكُمُ ٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَٱللَّهُ أَعْلَمُ بِإِيمَٰنِكُم بَعْضُكُم مِّنۢ بَعْضٍ فَٱنكِحُوهُنَّ بِإِذْنِ أَهْلِهِنَّ وَءَاتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ بِٱلْمَعْرُوفِ مُحْصَنَٰتٍ غَيْرَ مُسَٰفِحَٰتٍ وَلَا مُتَّخِذَٰتِ أَخْدَانٍ فَإِذَآ أُحْصِنَّ فَإِنْ أَتَيْنَ بِفَٰحِشَةٍ فَعَلَيْهِنَّ نِصْفُ مَا عَلَى ٱلْمُحْصَنَٰتِ مِنَ ٱلْعَذَابِ ذَٰلِكَ لِمَنْ خَشِىَ ٱلْعَنَتَ مِنكُمْ وَأَن تَصْبِرُوا۟ خَيْرٌ لَّكُمْ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy25. (ወንዶች ሆይ!) ከናንተ መካከል ጥብቆች ምዕመናትን ለማግባት ሀብትን ያልቻለ ሰው እጆቻችሁ ንብረት ካደረጓቸው ከምዕመናት መካከል ወጣቶቻችሁን አገልጋዬች የመረጠውን ያግባ:: አላህ የውስጥ እምነታችሁን ምንነት አዋቂ ነውና:: ከፊላችሁ ከከፊሉ የተራባ ነው:: ባሮችንም ቢሆን እንደዚሁ በአሳዳሪዎቻቸው ፈቃድ ብቻ አግቧቸው:: መህሮቻቸውንም በመልካም መንገድ ስጧቸው:: ጥብቆች ሆነው ዝሙተኛ ያልሆኑ የስርቆሽ ወዳጅንም ያልያዙ እንደሆኑ አግቧቸው:: በማግባት በተጠበቁም ጊዜ መጥፎን ስራ ቢሰሩ በእነርሱ ላይ የተደነገገው ቅጣት በነፃዎቹ ላይ ከተደነገገው ቅጣት ግማሹ ቅጣት አለባቸው:: ያ ከናንተ መካከል ዝሙትን ለፈራ ብቻ ነው:: መታገሳችሁ የተሻለ ነው:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከናንተም ውስጥ ጥብቆች ምእምናት የኾኑትን ለማግባት ሀብትን ያልቻለ ሰው እጆቻችሁ ንብረት ካደረጓቸው ከምእምናት ወጣቶቻችሁ (ባሪያን ያግባ)፡፡ አላህም እምነታችሁን ዐዋቂ ነው፡፡ ከፊላችሁ ከከፊሉ (የተራባ) ነው፡፡ (ባሮችን) በጌቶቻቸውም ፈቃድ አግቡዋቸው፡፡ መህሮቻቸውንም በመልካም መንገድ ስጧቸው፡፡ ጥብቆች ኾነው ዝሙተኞች ያልኾኑ የስርቆሽ ወዳጆችንም ያልያዙ ሲኾኑ (አግቧቸው)፡፡ በማግባት በተጠበቁም ጊዜ መጥፎን ሥራ ቢሠሩ በእነርሱ ላይ ከቅጣት በነጻዎቹ ላይ ያለው ግማሽ አለባቸው፡፡ ይኸ (ባሪያን ማግባት) ከናንተ ዝሙትን ለፈራ ሰው ነው፡፡ መታገሳችሁ ለናንተ በላጭ ነው። አላህም መሓሪ አዛኝ ነው።