caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Nisaa፣ አንቀጽ 3

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 92 · 4:3

وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا۟ فِى ٱلْيَتَٰمَىٰ فَٱنكِحُوا۟ مَا طَابَ لَكُم مِّنَ ٱلنِّسَآءِ مَثْنَىٰ وَثُلَٰثَ وَرُبَٰعَ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا۟ فَوَٰحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُكُمْ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰٓ أَلَّا تَعُولُوا۟

Amharic Translation - Africa Academy3. (እናንተ ሙስሊም ወንዶች ሆይ) በናንተ ስር ያሉት ሴት የቲሞችን በማግባታችሁ አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ ከሴቶች መካከል ለእናንተ የመረጣችሁትን (ደስ ያሏችሁን) ሁለት ሁለት ሶስት ሶስትና አራት አራት አግቡ:: በሚስቶች መካከል አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ ግን አንዲትን ሴት ብቻ ወይም ንብረታችሁ የሆኑት ሴት ባሪያዎችን ብቻ (በሚስትነት) ያዙ:: ይህም (ሴትን ልጅ) እንዳትበድሉ በጣም የቀረበ ተግባር ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበየቲሞችም (ማግባት) አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ (ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ)፡፡ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ (አግቡ) ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70