caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Nisaa፣ አንቀጽ 24

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 92 · 4:24

وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلنِّسَآءِ إِلَّا مَا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُكُمْ كِتَٰبَ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْ وَأُحِلَّ لَكُم مَّا وَرَآءَ ذَٰلِكُمْ أَن تَبْتَغُوا۟ بِأَمْوَٰلِكُم مُّحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَٰفِحِينَ فَمَا ٱسْتَمْتَعْتُم بِهِۦ مِنْهُنَّ فَـَٔاتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ فَرِيضَةً وَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ فِيمَا تَرَٰضَيْتُم بِهِۦ مِنۢ بَعْدِ ٱلْفَرِيضَةِ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy24. ባል ያገቡ ሴቶችም በጦርነት እጆቻችሁ በምርኮ የያዟቸው ሲቀሩ (በእናንተ ላይ እርም ናቸው):: ይህን ህግ አላህ በእናንተ ላይ ደነገገ:: ከነዚህ ከተከለከሉት ሌላ ጥብቆች ሆናችሁና ዝሙተኞች ሳትሆኑ በገንዘባችሁ ጋብቻን ልትፈለጉ ለእናንተ ተፈቀደ:: እናም ከእነርሱም መገናኘት የተጠቀማችሁባቸውን ሴቶች መህሮቻቸውን ልትሰጧቸው ግዴታ ነው:: ከመወሰን በኋላ በተዋደዳችሁበት ነገር በእናንተ ላይ ኃጢአት የለም:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከሴቶችም (በባል) ጥብቆቹ እጆቻቸሁ (በምርኮ) የያዙዋቸው ሲቀሩ በእናንተ ላይ እርም ናቸው፡፡ (ይህን) አላህ በናንተ ላይ ጻፈ፡፡ ከዚሃችሁም (ከተከለከሉት) ወዲያ ጥብቆች ኾናችሁ ዝሙተኞች ሳትኾኑ በገንዘቦቻችሁ ልትፈልጉ ለእናንተ ተፈቀደ፡፡ ከእነሱም በርሱ (በመገናኘት) የተጠቀማችሁባቸውን ሴቶች መህሮቻቸውን ግዴታ ሲኾን ስጧቸው፡፡ ከመወሰንም በኋላ በተዋደዳችሁበት ነገር በእናንተ ላይ ኀጢአት የለም፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70