يَسْـَٔلُكَ أَهْلُ ٱلْكِتَٰبِ أَن تُنَزِّلَ عَلَيْهِمْ كِتَٰبًا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ فَقَدْ سَأَلُوا۟ مُوسَىٰٓ أَكْبَرَ مِن ذَٰلِكَ فَقَالُوٓا۟ أَرِنَا ٱللَّهَ جَهْرَةً فَأَخَذَتْهُمُ ٱلصَّٰعِقَةُ بِظُلْمِهِمْ ثُمَّ ٱتَّخَذُوا۟ ٱلْعِجْلَ مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَتْهُمُ ٱلْبَيِّنَٰتُ فَعَفَوْنَا عَن ذَٰلِكَ وَءَاتَيْنَا مُوسَىٰ سُلْطَٰنًا مُّبِينًا
Amharic Translation - Africa Academy153. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመጽሐፉ ባለቤቶች እነርሱ ላይ ከሰማይ መጽሐፍን እንድታወርድ ይጠይቁሃል:: ከዚህም የከበደን ጥያቄ ከዚህ በፊት ሙሳን በእርግጥ ጠይቀዋል:: «አላህን በግልጽ አሳየን።» ብለዋል:: በበደላቸዉም ምክንያት መብረቅ ያዘቻቸው:: ከዚያም ተዓምራት ከመጡላቸው በኋላ ወይፈኑን አምላክ አድረገው ያዙ:: ከዚያ ያንን ይቅር አልን:: ሙሳንም ግልጽ ስልጣን ሰጠነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየመጽሐፉ ሰዎች በነሱ ላይ ከሰማይ መጽሐፍን እንድታወርድ ይጠይቁሃል፡፡ ከዚያም የከበደን (ነገር) ሙሳን በእርግጥ ጠይቀዋል፡፡ «አላህንም በግልጽ አሳየን» ብለዋል፡፡ በበደላቸውም መብረቅ ያዘቻቸው፡፡ ከዚያም ተዓምራቶች ከመጡላቸው በኋላ ወይፈኑን (አምላክ አድርገው) ያዙ፡፡ ከዚያም ይቅር አልን፡፡ ሙሳንም ግልጽ ስልጣንን ሰጠነው፡፡