وَإِذَا كُنتَ فِيهِمْ فَأَقَمْتَ لَهُمُ ٱلصَّلَوٰةَ فَلْتَقُمْ طَآئِفَةٌ مِّنْهُم مَّعَكَ وَلْيَأْخُذُوٓا۟ أَسْلِحَتَهُمْ فَإِذَا سَجَدُوا۟ فَلْيَكُونُوا۟ مِن وَرَآئِكُمْ وَلْتَأْتِ طَآئِفَةٌ أُخْرَىٰ لَمْ يُصَلُّوا۟ فَلْيُصَلُّوا۟ مَعَكَ وَلْيَأْخُذُوا۟ حِذْرَهُمْ وَأَسْلِحَتَهُمْ وَدَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَوْ تَغْفُلُونَ عَنْ أَسْلِحَتِكُمْ وَأَمْتِعَتِكُمْ فَيَمِيلُونَ عَلَيْكُم مَّيْلَةً وَٰحِدَةً وَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ إِن كَانَ بِكُمْ أَذًى مِّن مَّطَرٍ أَوْ كُنتُم مَّرْضَىٰٓ أَن تَضَعُوٓا۟ أَسْلِحَتَكُمْ وَخُذُوا۟ حِذْرَكُمْ إِنَّ ٱللَّهَ أَعَدَّ لِلْكَٰفِرِينَ عَذَابًا مُّهِينًا
Amharic Translation - Africa Academy102.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ) በጦርነት ላይ በመካከላቸው በሆንክና ሶላትን ለእነርሱ ባሰገድካቸው ጊዜ ከእነርሱ አንዱ ቡድን ካንተ ጋር ይቁም:: መሳሪያዎቻቸውንም ይያዙ:: ሱጁድ ባደረጉ ጊዜ ከበስተኋላችሁ ይሁኑ:: ከዚያም እነዚያ ቡድኖች ወደ ግንባር ይሂዱና ያልሰገዱት ሌሎች ቡድኖች ይምጡ :: ከዚያም ካንተ ጋር ይስገዱ:: ጥንቃቄያቸውንና መሳሪያዎቻቸውንም ይያዙ:: እነዚያ በአላህ የካዱት ከትጥቅና ስንቃችሁ ብትዘናጉና በአንድ ጊዜ ቢወሯችሁ ይመኛሉ:: ዝናብ አውኳችሁ ወይም በሽተኛ ሆናችሁ ትጥቃችሁን ብታስቀምጡ በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም:: ጥንቃቄ አድርጉ:: አላህ ለካሐዲያን ሁሉ አዋራጅን ቅጣት አዘጋጀ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበውስጣቸውም በኾንክና ሶላትን ለእነርሱ ባስገደድካቸው ጊዜ ከእነሱ አንዲት ጭፍራ ካንተ ጋር ትቁም፡፡ መሣሪያዎቻቸውንም ይያዙ፡፡ በግንባራቸውም በተደፉ ጊዜ ከስተኋላችሁ ይኹኑ፡፡ (እነዚህ ይኺዱና) ያልሰገዱትም ሌሎቹ ጭፍሮች ይምጡ፡፡ ከአንተም ጋር ይስገዱ፡፡ ጥንቃቄያቸውንና መሣሪያዎቻቸውንም ይያዙ፡፡ እነዚያ የካዱት ከመሣሪያዎቻችሁና ከጓዞቻችሁ ብትዘነጉና በእናንተ ላይ አንዲትን መዘንበል ቢዘነበሉ ተመኙ፡፡ ከዝናብም የኾነ ችግር በእናንተ ቢኖር ወይም ሕመምተኞች ብትኾኑ መሣሪያዎቻችሁን ብታስቀምጡ በናንተ ላይ ኀጢአት የለም፡፡ ጥንቃቄያችሁንም ያዙ፡፡ አላህ ለከሓዲዎች አዋራጅን ቅጣት አዘጋጀ፡፡