caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Nisaa፣ አንቀጽ 12

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 92 · 4:12

وَلَكُمْ نِصْفُ مَا تَرَكَ أَزْوَٰجُكُمْ إِن لَّمْ يَكُن لَّهُنَّ وَلَدٌ فَإِن كَانَ لَهُنَّ وَلَدٌ فَلَكُمُ ٱلرُّبُعُ مِمَّا تَرَكْنَ مِنۢ بَعْدِ وَصِيَّةٍ يُوصِينَ بِهَآ أَوْ دَيْنٍ وَلَهُنَّ ٱلرُّبُعُ مِمَّا تَرَكْتُمْ إِن لَّمْ يَكُن لَّكُمْ وَلَدٌ فَإِن كَانَ لَكُمْ وَلَدٌ فَلَهُنَّ ٱلثُّمُنُ مِمَّا تَرَكْتُم مِّنۢ بَعْدِ وَصِيَّةٍ تُوصُونَ بِهَآ أَوْ دَيْنٍ وَإِن كَانَ رَجُلٌ يُورَثُ كَلَٰلَةً أَوِ ٱمْرَأَةٌ وَلَهُۥٓ أَخٌ أَوْ أُخْتٌ فَلِكُلِّ وَٰحِدٍ مِّنْهُمَا ٱلسُّدُسُ فَإِن كَانُوٓا۟ أَكْثَرَ مِن ذَٰلِكَ فَهُمْ شُرَكَآءُ فِى ٱلثُّلُثِ مِنۢ بَعْدِ وَصِيَّةٍ يُوصَىٰ بِهَآ أَوْ دَيْنٍ غَيْرَ مُضَآرٍّ وَصِيَّةً مِّنَ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy12. ለእናንተም ሚስቶቻችሁ ከተውት ንብረት ለእነርሱ ልጅ ካልኖራቸው ግማሹ አላችሁ:: ለእነርሱም ልጅ ቢኖራቸው ከተውት ሀብት ከአራት አንድ አላችሁ :: (ይህም) በእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከእዳ ክፍያ በኋላ ነው:: ለእናንተም ልጅ ከሌላችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ (ለሚስቶቻችሁ) አንድ አራተኛ አላቸው። ለእናንተም ልጅ ባይኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ (ለሚስቶቻችሁ) ከስምንት አንድ አላቸው:: (ይህም) ከምትናዘዙበት ኑዛዜ ወይም ከእዳ ክፍያ በኋላ ነው:: ወላጆችም ልጅም የሌለውና የጎን ወራሾች የሚወርሱት ወንድ ወይም ሴት ቢገኝ ለእርሱም (ለሟቹ) ከእናቱ በኩል ብቻ የሆኑ ወንድም ወይም እህት ቢኖሩት ከሁለቱ ለእያንደንዳቸው ከስድስት አንድ አላቸው:: ከአንድ የበዙ ቢሆኑ ደግሞ በሲሶው ላይ ተጋሪዎች ናቸው:: ይህም ወራሾቹን የማይጎዳ ሆኖ ከእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከእዳ በኋላ ነው:: ከአላህም የሆነን ኑዛዜ ያዛችኋል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ቻይ ነውና።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለእናንተም ሚስቶቻችሁ ከተዉት ንብረት ለእነርሱ ልጅ ባይኖራቸው ግማሹ አላችሁ፡፡ ለእነሱም ልጅ ቢኖራቸው ከተዉት ሀብት ከአራት አንድ አላችሁ፡፡ (ይህም) በእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከዕዳ በኋላ ነው፡፡ ለናንተም ልጅ ባይኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ (ለሚስቶች) ከአራት አንድ አላቸው፡፡ ለእናንተም ልጅ ቢኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ ከስምንት አንድ አላቸው ይህም በርሷ ከምትናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከዕዳ በኋላ ነው፡፡ ወላጅም ልጅም የሌለው በጎን ወራሾች የሚወርስ ወንድ ወይም ሴት ቢገኝ ለእርሱም (ለሟቹ) ወንድም ወይም እኅት (ከእናቱ በኩል ብቻ የኾነ) ቢኖር ከሁለቱ ለያንዳንዳቸው ከስድስት አንድ አላቸው፡፡ ከዚህም (ከአንድ) የበዙ ቢኾኑ እነርሱ በሲሶው ተጋሪዎች ናቸው፡፡ (ይህም ወራሾችን) የማይጎዳ ኾኖ በእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከዕዳ በኋላ ነው፡፡ ከአላህም የኾነን ኑዛዜ (ያዛችኋል)፡፡ አላህም ዐዋቂ ቻይ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70