يَسْتَفْتُونَكَ قُلِ ٱللَّهُ يُفْتِيكُمْ فِى ٱلْكَلَٰلَةِ إِنِ ٱمْرُؤٌا۟ هَلَكَ لَيْسَ لَهُۥ وَلَدٌ وَلَهُۥٓ أُخْتٌ فَلَهَا نِصْفُ مَا تَرَكَ وَهُوَ يَرِثُهَآ إِن لَّمْ يَكُن لَّهَا وَلَدٌ فَإِن كَانَتَا ٱثْنَتَيْنِ فَلَهُمَا ٱلثُّلُثَانِ مِمَّا تَرَكَ وَإِن كَانُوٓا۟ إِخْوَةً رِّجَالًا وَنِسَآءً فَلِلذَّكَرِ مِثْلُ حَظِّ ٱلْأُنثَيَيْنِ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمْ أَن تَضِلُّوا۟ وَٱللَّهُ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۢ
Amharic Translation - Africa Academy176. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይጠይቁሃል: «ወላጆችና ልጅ ሳይኖረው በሚወረስ ሟች ሰው ጉዳይ አላህ ይነግራችኋል።» በላቸው፡፡ ልጅ የሌለው ሰው ቢሞትና ለእርሱ እህት ብትኖረው ለእርሷ ከተወው ንብረት ግማሽ አላት፡፡ እርሱም ለእርሷ ልጅ የሌላት እንደሆነች በሙሉ ይወርሳታል፡፡ ሁለት እህቶች ወይም ከሁለት በላይ ቢሆኑ ግን ከተወው ንብረት ከሶስት ሁለት እጅ አላቸው ፡፡ ወንድሞችና እህቶች ወንዶችና ሴቶች ቢሆኑ ደግሞ ለወንድ የሁለት ሴቶች ድርሻ ያህል አለው ፡፡ አላህ እንዳትሳሳቱ ህግጋትን ለእናንተ ያብራራል ፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነውና፡፡
Amharic Translation - Muhammad Sadiqይጠይቁሃል በላቸው፡- «ወላጅና ልጅ ሳይኖረው በሚወረስ ሰው አላህ ይነግራችኋል፡፡ ለእርሱ ልጅ የሌለው ሰው ቢሞት ለእርሱም እኅት ብትኖረው ለእርስዋ ከተወው ረጀት ግማሹ አላት፡፡ እርሱም ለርሷ ልጅ የሌላት እንደኾነች (በሙሉ) ይወርሳታል፡፡ ሁለት (እኅቶች ወይም ከሁለት በላይ) ቢኾኑም ከተወው ረጀት ከሦስት ሁለት እጁ አላቸው፡፡ ወንድሞች (ና እኅቶች) ወንዶችና ሴቶች ቢኾኑም ለወንዱ የሁለት ሴቶች ድርሻ ብጤ አለው፡፡ አላህ እንዳትሳሳቱ ለእናንተ ያብራራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡»