وَٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا۟ بِهِۦ شَيْـًٔا وَبِٱلْوَٰلِدَيْنِ إِحْسَٰنًا وَبِذِى ٱلْقُرْبَىٰ وَٱلْيَتَٰمَىٰ وَٱلْمَسَٰكِينِ وَٱلْجَارِ ذِى ٱلْقُرْبَىٰ وَٱلْجَارِ ٱلْجُنُبِ وَٱلصَّاحِبِ بِٱلْجَنۢبِ وَٱبْنِ ٱلسَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُكُمْ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا
Amharic Translation - Africa Academy36. አላህን ተገዙ:: በእርሱ ምንንም አታጋሩ። ለወላጆች፣ ለቅርብ ዝምድና ባለቤቶች፣ ለየቲሞች፣ ለምስኪኖች፣ ለቅርብ ጎረቤት፣ ለሩቅ ጎረቤት፣ ለጎን ባልደረባ፣ ለመንገደኛ፣ እጆቻችሁ ንብረት ላደረጓቸው ባሮች መልካምን ስሩ። አላህ ኩራተኞችንና ጉረኞችን አይወድምና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህንም ተገዙ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ በወላጆችና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው (ባሮች)፣ መልካምን (ሥሩ)፤ አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡