caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Nisaa፣ አንቀጽ 43

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 92 · 4:43

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَقْرَبُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَأَنتُمْ سُكَٰرَىٰ حَتَّىٰ تَعْلَمُوا۟ مَا تَقُولُونَ وَلَا جُنُبًا إِلَّا عَابِرِى سَبِيلٍ حَتَّىٰ تَغْتَسِلُوا۟ وَإِن كُنتُم مَّرْضَىٰٓ أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ أَوْ جَآءَ أَحَدٌ مِّنكُم مِّنَ ٱلْغَآئِطِ أَوْ لَٰمَسْتُمُ ٱلنِّسَآءَ فَلَمْ تَجِدُوا۟ مَآءً فَتَيَمَّمُوا۟ صَعِيدًا طَيِّبًا فَٱمْسَحُوا۟ بِوُجُوهِكُمْ وَأَيْدِيكُمْ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَفُوًّا غَفُورًا

Amharic Translation - Africa Academy43. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የምትሉትን ነገር ለይታችሁ አስከምታውቁ ድረስ የሰከራችሁ ሆናችሁ ወደ ሶላት አትቅረቡ:: ጀናባ ስትሆኑም መንገድን አላፊዎች ካልሆናችሁ በስተቀር ሙሉ አካላታችሁን እስከምትታጥቡ ድረስ መስጊድን አትቅረቡ:: በሽተኞች ወይም በጉዞ ላይ ብትሆኑ ወይም ከናንተ አንዱ ከአይነ ምድር ቢጸዳዳ ወይም ከሴቶች ጋር ብትነካኩና ( የግብረስጋ ግንኙነት ብትፈጽሙና) ውሃን ባታገኙ ንጹህ የሆነን የምድር ገጽ (አፈርን) አብሱ:: ከዚያ ፊቶቻችሁንና እጆቻችሁን በእርሱ አብሱ:: አላህ ይቅር ባይና መሀሪ ነውና።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! እናንተ የሰከራችሁ ኾናችሁ የምትሉትን ነገር እስከምታውቁ የረከሳችሁም ስትኾኑ መንገድን አላፊዎች ካልኾናችሁ በስተቀር (አካላታችሁን) እስከምትታጠቡ ድረስ ስግደትን አትቅረቡ፡፡ በሽተኞች ወይም በጉዞ ላይ ብትኾኑም፥ ወይንም ከእናንተ አንዱ ከዓይነምድር ቢመጣ፥ ወይንም ሴቶችን ብትነካኩና ውሃን ባታገኙ፣ ንጹሕ የኾነን የምድር ገጽ አስቡ፡፡ ፊቶቻችሁንና እጆቻችሁንም (በርሱ) አብሱ፡፡ አላህ ይቅር ባይ መሓሪ ነውና፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70