وَٱبْتَلُوا۟ ٱلْيَتَٰمَىٰ حَتَّىٰٓ إِذَا بَلَغُوا۟ ٱلنِّكَاحَ فَإِنْ ءَانَسْتُم مِّنْهُمْ رُشْدًا فَٱدْفَعُوٓا۟ إِلَيْهِمْ أَمْوَٰلَهُمْ وَلَا تَأْكُلُوهَآ إِسْرَافًا وَبِدَارًا أَن يَكْبَرُوا۟ وَمَن كَانَ غَنِيًّا فَلْيَسْتَعْفِفْ وَمَن كَانَ فَقِيرًا فَلْيَأْكُلْ بِٱلْمَعْرُوفِ فَإِذَا دَفَعْتُمْ إِلَيْهِمْ أَمْوَٰلَهُمْ فَأَشْهِدُوا۟ عَلَيْهِمْ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ حَسِيبًا
Amharic Translation - Africa Academy6. (ሙስሊሞች ሆይ!) የቲሞችን ለጋብቻ እስከደረሱ ድረስ ፈትኗቸው:: ከእነርሱም ብልህነትን ብታውቁ ገንዘቦቻቸውን ስጧቸው:: በማባከንና ማደጋቸውን በመሽቀዳደም ገንዘቦቻቸውን አትብሉባቸው:: (ከአሳዳጊዎቹ መካከል) ሀብታም የሆነ ሰው ከገንዘቦቻቸው (ቅንጣት ያህል እንኳን ከመቅረብ) ይከልከል:: ደሃ የሆነ ሰዉም ቢሆን ለድካሙ ብቻ በአግባቡ ይብላ:: ገንዘቦቻቸውን ወደ እነርሱ በሰጣችሁም ጊዜ በእነርሱ ላይ አስመስክሩ:: በተጠባባቂነትም አላህ በቂ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየቲሞችንም ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ ድረስ ፈትኑዋቸው፡፡ ከእነርሱም ቅንነትን ብታውቁ ገንዘቦቻቸውን ወደ እነርሱ ስጡ፡፡ በማባከንና ማደጋቸውንም በመሽቀዳደም አትብሏት፡፡ (ከዋቢዎች) ሀብታምም የኾነ ሰው ይከልከል፡፡ ድሃም የኾነ ሰው (ለድካሙ) በአግባብ ይብላ፡፡ ገንዘቦቻቸውንም ወደ እነርሱ በሰጣችሁ ጊዜ በእነርሱ ላይ አስመስክሩ፡፡ ተጠባባቂነትም በአላህ በቃ፡፡