ሱረቱ Al-Hijr الحجر
99 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 54
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ الٓر تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱلْكِتَٰبِ وَقُرْءَانٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy1. አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤ እነዚህ አናቅጽ ከመጽሐፍ አናቅጽና ገላጭ ከሆነው ቁርኣን ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رُّبَمَا يَوَدُّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَوْ كَانُوا۟ مُسْلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy2.እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች በትንሳኤ ቀን ሙስሊሞች በሆኑ ኖሮ ብለው በብዛት ይመኛሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَرْهُمْ يَأْكُلُوا۟ وَيَتَمَتَّعُوا۟ وَيُلْهِهِمُ ٱلْأَمَلُ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ተዋቸው:: ይብሉ ይጠቀሙም:: ተስፋም ያዘናጋቸው:: በእርግጥም መጥፎ ፍጻሜያቸውን ያውቃሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَآ أَهْلَكْنَا مِن قَرْيَةٍ إِلَّا وَلَهَا كِتَابٌ مَّعْلُومٌ
Amharic Translation - Africa Academy4. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ማንኛይቱንም ከተማ ለእርሷ የተወሰነ መጽሐፍ ጊዜያት ያላት ሆና እንጂ አላጠፋንም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَّا تَسْبِقُ مِنْ أُمَّةٍ أَجَلَهَا وَمَا يَسْتَـْٔخِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy5. ማንኛይቱም ሕዝብ የመጥፊያ ጊዜዋን በምንም ዘዴ አትቀድምም:: ከእርሱም በማንም ሀይል አትዘገይምም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِى نُزِّلَ عَلَيْهِ ٱلذِّكْرُ إِنَّكَ لَمَجْنُونٌ
Amharic Translation - Africa Academy6. እነዚያ የመካ ከሓዲያን አሉ: «አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ! አንተ በእርግጥ እብድ ነህ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَّوْ مَا تَأْتِينَا بِٱلْمَلَٰٓئِكَةِ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy7. «ከእውነተኞቹ እንደ ሆንክ መስካሪ መላዕክት ለምን አታመጣልንም?» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا نُنَزِّلُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ إِلَّا بِٱلْحَقِّ وَمَا كَانُوٓا۟ إِذًا مُّنظَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy8. መላእክትን ደግሞ በእውነት በቅጣት እንጂ አናወርድም:: ያን ጊዜም የሚቆዩ ጊዜ የሚሰጣቸው አይደሉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا ٱلذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ
Amharic Translation - Africa Academy9. እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው:: እኛም ጠባቂዎቹ ነን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ فِى شِيَعِ ٱلْأَوَّلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተም በፊት በነበሩት በመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ውስጥ መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል:
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا يَأْتِيهِم مِّن رَّسُولٍ إِلَّا كَانُوا۟ بِهِۦ يَسْتَهْزِءُونَ
Amharic Translation - Africa Academy11. ማንኛዉም መልዕክተኛ በእርሱ የሚያላግጡበት ሆነው እንጂ አይመጣላቸዉም ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَذَٰلِكَ نَسْلُكُهُۥ فِى قُلُوبِ ٱلْمُجْرِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy12. ልክ እንደዚሁ ማስተባበልን በአመጸኞች ልቦች ውስጥ እናስገባዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَا يُؤْمِنُونَ بِهِۦ وَقَدْ خَلَتْ سُنَّةُ ٱلْأَوَّلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy13. በእርሱ አያምኑበትም፤ የቀድሞዎቹም ድርጊት በእርግጥ አልፋለች (እንደጠፉ ይጠፋሉ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ فَتَحْنَا عَلَيْهِم بَابًا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ فَظَلُّوا۟ فِيهِ يَعْرُجُونَ
Amharic Translation - Africa Academy14. በእነርሱም ላይ ከሰማይ ደጃፍን በከፈትንላቸውና በእርሱ ሲወጡ ቢውሉም
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَقَالُوٓا۟ إِنَّمَا سُكِّرَتْ أَبْصَٰرُنَا بَلْ نَحْنُ قَوْمٌ مَّسْحُورُونَ
Amharic Translation - Africa Academy15. «የተዘጉ ዓይኖቻችን ተጭበርብረው ነው:: እንዲያዉም እኛ የተደገመብን ሰዎች ነን።» ባሉ ነበር።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ جَعَلْنَا فِى ٱلسَّمَآءِ بُرُوجًا وَزَيَّنَّٰهَا لِلنَّٰظِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy16. በሰማይም ላይ ከዋክብቶችን በእርግጥ አድርገናል (ፈጥረናል):: ለተመልካቾችም በከዋክብት አጊጠናታል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَحَفِظْنَٰهَا مِن كُلِّ شَيْطَٰنٍ رَّجِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy17. ከተባረረ ሰይጣንም ሁሉ ጠብቀናታል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا مَنِ ٱسْتَرَقَ ٱلسَّمْعَ فَأَتْبَعَهُۥ شِهَابٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy18. ግን ወሬ መስማትን የሚሰርቅ ወዲያውኑ አብሪ ችቦ ይከተለዋል:: (ያቃጥለዋል)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلْأَرْضَ مَدَدْنَٰهَا وَأَلْقَيْنَا فِيهَا رَوَٰسِىَ وَأَنۢبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ شَىْءٍ مَّوْزُونٍ
Amharic Translation - Africa Academy19. ምድርንም ዘረጋናት:: በውስጧም ኮረብታዎችን ጣልንባት:: በውስጧም የተለካን በቃይ ሁሉ አበቀልንባት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَعَلْنَا لَكُمْ فِيهَا مَعَٰيِشَ وَمَن لَّسْتُمْ لَهُۥ بِرَٰزِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy20.(ሰዎች ሆይ!) በእርሷ ውስጥ ለእናንተ ልዩ ልዩ መኖሪያዎችንና ለእርሱ መጋቢዎቹ ያልሆናችሁትንም እንስሳትን አደረግንላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن مِّن شَىْءٍ إِلَّا عِندَنَا خَزَآئِنُهُۥ وَمَا نُنَزِّلُهُۥٓ إِلَّا بِقَدَرٍ مَّعْلُومٍ
Amharic Translation - Africa Academy21. መጋዘኖቹም መክፈቻቸው እኛው ዘንድ ያልሆነ ምንም ነገር የለም:: በተወሰነም ልክ እንጂ አናወርደዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَرْسَلْنَا ٱلرِّيَٰحَ لَوَٰقِحَ فَأَنزَلْنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَأَسْقَيْنَٰكُمُوهُ وَمَآ أَنتُمْ لَهُۥ بِخَٰزِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy22. ንፋስን ደመናን ተሸካሚዎች አድርገን ላክን:: ከሰማይም ከደመና ዝናብን አወረድን:: እርሱንም አጠጣናችሁ:: እናንተ ለእርሱ አድላቢዎች (አከማቾች) አይደላችሁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّا لَنَحْنُ نُحْىِۦ وَنُمِيتُ وَنَحْنُ ٱلْوَٰرِثُونَ
Amharic Translation - Africa Academy23. እኛ ሕያው የምናደርግና የምንገድል እኛው ብቻ ነን:: እኛው ፍጡርን ሁሉ የምንወርስ ቀሪ ነን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ عَلِمْنَا ٱلْمُسْتَقْدِمِينَ مِنكُمْ وَلَقَدْ عَلِمْنَا ٱلْمُسْتَـْٔخِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy24. ከናንተም ተቀዳሚዎቹን በእርግጥ አውቀናል:: ወደ ኋላ ቀሪዎቹንም በእርግጥ አውቀናል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّ رَبَّكَ هُوَ يَحْشُرُهُمْ إِنَّهُۥ حَكِيمٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)ጌታህ ይሰበስባቸዋል:: እርሱ ጥበበኛና ሁሉን አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ خَلَقْنَا ٱلْإِنسَٰنَ مِن صَلْصَٰلٍ مِّنْ حَمَإٍ مَّسْنُونٍ
Amharic Translation - Africa Academy26. ሰውንም ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጥቁር ጭቃ በእርግጥ ፈጠርነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلْجَآنَّ خَلَقْنَٰهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ ٱلسَّمُومِ
Amharic Translation - Africa Academy27. ጃንን ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَٰٓئِكَةِ إِنِّى خَٰلِقٌۢ بَشَرًا مِّن صَلْصَٰلٍ مِّنْ حَمَإٍ مَّسْنُونٍ
Amharic Translation - Africa Academy28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ለመላዕክት ባለ ጊዜ (የሆነውን አስታውስ): «እኔ ሰውን ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጭቃ እፈጥራለሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِذَا سَوَّيْتُهُۥ وَنَفَخْتُ فِيهِ مِن رُّوحِى فَقَعُوا۟ لَهُۥ سَٰجِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy29. «ፍጥረቱን ባስተካከልኩትና በውስጡ ከመንፈሴ በነፋሁበትም ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ሆናችሁ ውደቁ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَسَجَدَ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ كُلُّهُمْ أَجْمَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy30. መላዓክትም ሁሉም ተሰብስበው ሰገዱ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّآ إِبْلِيسَ أَبَىٰٓ أَن يَكُونَ مَعَ ٱلسَّٰجِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy31. ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር:: እርሱማ ከሰጋጆቹ ጋር ከመሆን እንቢ አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا لَكَ أَلَّا تَكُونَ مَعَ ٱلسَّٰجِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy32. አላህም፡ «ዲያብሎስ ሆይ! ከሰጋጆቹ ጋር የማትሆን ላንተ ምን ምክንያት አለህ?» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ لَمْ أَكُن لِّأَسْجُدَ لِبَشَرٍ خَلَقْتَهُۥ مِن صَلْصَٰلٍ مِّنْ حَمَإٍ مَّسْنُونٍ
Amharic Translation - Africa Academy33. «ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከግም ጭቃ ለፈጠርከው ሰው ልሰግድ አይገባኝም።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فَٱخْرُجْ مِنْهَا فَإِنَّكَ رَجِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy34. አላህም አለው: «ከእርሷም ውጣ አንተ የተባረርክ እርጉም ነህና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّ عَلَيْكَ ٱللَّعْنَةَ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلدِّينِ
Amharic Translation - Africa Academy35. «ባንተ ላይም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ እርግማን አለብህ።» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ رَبِّ فَأَنظِرْنِىٓ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ
Amharic Translation - Africa Academy36. «ጌታዬ ሆይ! እንግዲያውስ እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝ።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فَإِنَّكَ مِنَ ٱلْمُنظَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy37. አላህም አለ፡- «አንተ ከሚቆዩት ነህ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْوَقْتِ ٱلْمَعْلُومِ
Amharic Translation - Africa Academy38. «እስከታወቀው ቀን ድረስ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ رَبِّ بِمَآ أَغْوَيْتَنِى لَأُزَيِّنَنَّ لَهُمْ فِى ٱلْأَرْضِ وَلَأُغْوِيَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy39. ዲያብሎስም አለ፡- «ጌታዬ ሆይ! እኔን በማጥመምህ ይሁንብኝ ለእነርሱ በምድር ላይ ኃጢአትን እሸልምላቸዋለሁ። ሁላቸውንም አጠማቸዋለሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا عِبَادَكَ مِنْهُمُ ٱلْمُخْلَصِينَ
Amharic Translation - Africa Academy40. «ከእነርሱ ፍጹሞቹ ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ هَٰذَا صِرَٰطٌ عَلَىَّ مُسْتَقِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy41. አላህም አለ፡- «ይህ በእኔ ላይ መጠበቁ የተገባ ቀጥተኛ መንገድ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ عِبَادِى لَيْسَ لَكَ عَلَيْهِمْ سُلْطَٰنٌ إِلَّا مَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلْغَاوِينَ
Amharic Translation - Africa Academy42. «እነሆ ባሮቼ! በእነርሱ ላይ አንተ ስልጣን የለህም። ከጠማሞች የተከተለህ ሰው ብቻ ሲቀር።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمَوْعِدُهُمْ أَجْمَعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy43. «ገሀነምም ለእርሱና ለተከተሉት ለሁሉም በእርግጥ ቀጠሯቸው ናት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَهَا سَبْعَةُ أَبْوَٰبٍ لِّكُلِّ بَابٍ مِّنْهُمْ جُزْءٌ مَّقْسُومٌ
Amharic Translation - Africa Academy44. «ለእርሷ ሰባት በሮች (ደጃፎች ) አሏት። ለየበሮቹም ሁሉ ከሰይጣናት ቡድኖች የተከፋፈለ ድርሻ አለ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلْمُتَّقِينَ فِى جَنَّٰتٍ وَعُيُونٍ
Amharic Translation - Africa Academy45. እነዚያ ከኃጢአት የተጠነቀቁት በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱدْخُلُوهَا بِسَلَٰمٍ ءَامِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy46. «ጸጥተኞች ሆናችሁ በሰላም ግቧት።» ይባላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَزَعْنَا مَا فِى صُدُورِهِم مِّنْ غِلٍّ إِخْوَٰنًا عَلَىٰ سُرُرٍ مُّتَقَٰبِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy47. በአልጋዎችም ላይ ፊት ለፊት የሚተያዩ ወንድማማቾች ሆነው በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ቂም ሁሉ እናስወግዳለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَا يَمَسُّهُمْ فِيهَا نَصَبٌ وَمَا هُم مِّنْهَا بِمُخْرَجِينَ
Amharic Translation - Africa Academy48. በእርሷም ውስጥ ምንም ድካም አይነካቸዉም፤ እነርሱም ከእርሷ ለምንጊዜም የሚወጡ አይደሉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
نَبِّئْ عِبَادِىٓ أَنِّىٓ أَنَا ٱلْغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መሃሪና አዛኝ እኔው ብቻ መሆኔን ለባሮቼ ንገር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّ عَذَابِى هُوَ ٱلْعَذَابُ ٱلْأَلِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy50. ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መሆኑንም ንገራቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَبِّئْهُمْ عَن ضَيْفِ إِبْرَٰهِيمَ
Amharic Translation - Africa Academy51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከኢብራሂም እንግዶችም ወሬ ንገራቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ دَخَلُوا۟ عَلَيْهِ فَقَالُوا۟ سَلَٰمًا قَالَ إِنَّا مِنكُمْ وَجِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy52. በእርሱ ላይ በገቡና ሰላም ባሉት ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: እርሱም፡- «እኛ ከናንተ ፈሪዎች ነን።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ لَا تَوْجَلْ إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَٰمٍ عَلِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy53. «አትፍራ እኛ አዋቂ በሆነ ወንድ ልጅ እናበስርሃለን።» አሉት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ أَبَشَّرْتُمُونِى عَلَىٰٓ أَن مَّسَّنِىَ ٱلْكِبَرُ فَبِمَ تُبَشِّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy54. «እርጅና የደረሰብኝ ከመሆኔ ጋር አበሰራችሁኝን? በምን ታበስሩኛላችሁ?» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ بَشَّرْنَٰكَ بِٱلْحَقِّ فَلَا تَكُن مِّنَ ٱلْقَٰنِطِينَ
Amharic Translation - Africa Academy55. «በእውነት አበሰርንህ ከተስፋ ቆራጮችም አትሁን።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ وَمَن يَقْنَطُ مِن رَّحْمَةِ رَبِّهِۦٓ إِلَّا ٱلضَّآلُّونَ
Amharic Translation - Africa Academy56. «ከጠማማዎችም በስተቀር ከጌታው እዝነት ተስፋን የሚቆርጥ ማነው?» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فَمَا خَطْبُكُمْ أَيُّهَا ٱلْمُرْسَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy57. «እናንተ መልዕክተኞች ሆይ! ኧረ ለመሆኑ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوٓا۟ إِنَّآ أُرْسِلْنَآ إِلَىٰ قَوْمٍ مُّجْرِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy58. አሉም: «እኛ አመፀኞች ወደ ሆኑ ሕዝቦች ተልከናል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّآ ءَالَ لُوطٍ إِنَّا لَمُنَجُّوهُمْ أَجْمَعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy59. «የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱን እኛ ሁላቸውንም በእርግጥ የምናድናቸው ነን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا ٱمْرَأَتَهُۥ قَدَّرْنَآ إِنَّهَا لَمِنَ ٱلْغَٰبِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy60. «ሚስቱ ብቻ ስትቀር።» (አሉ) እርሷንማ በቅጣቱ ውስጥ ከሚቀሩት ሰዎች መሆኗን ወስነናል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا جَآءَ ءَالَ لُوطٍ ٱلْمُرْسَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy61. መልዕክተኞቹም የሉጥን ቤተሰቦች በመጡባቸው ጊዜ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ إِنَّكُمْ قَوْمٌ مُّنكَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy62. ሉጥ «እናንተ የተሳሳታችሁ ሕዝቦች ናችሁ።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ بَلْ جِئْنَٰكَ بِمَا كَانُوا۟ فِيهِ يَمْتَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy63. አሉም: «አይደለም:: እኛ ህዝቦችህ በእሱ ይጠራጠሩበት በነበሩት ቅጣት መጣንልህ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَتَيْنَٰكَ بِٱلْحَقِّ وَإِنَّا لَصَٰدِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy64. «እውነትንም ይዘን መጣንልህ:: እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَسْرِ بِأَهْلِكَ بِقِطْعٍ مِّنَ ٱلَّيْلِ وَٱتَّبِعْ أَدْبَٰرَهُمْ وَلَا يَلْتَفِتْ مِنكُمْ أَحَدٌ وَٱمْضُوا۟ حَيْثُ تُؤْمَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy65. «ከቤተሰብህ ጋር በሌሊቱ ከፊል (አጋማሽ) ላይ ሂድ:: በኋላቸዉም ተከተል:: ከናንተም አንድም ሰው ወደ ኋላው አይገላመጥ:: ወደ ታዘዛችሁበትም ስፍራ እለፉ።» አሉት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَضَيْنَآ إِلَيْهِ ذَٰلِكَ ٱلْأَمْرَ أَنَّ دَابِرَ هَٰٓؤُلَآءِ مَقْطُوعٌ مُّصْبِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy66. ወደ እርሱም ያንን ትዕዛዝ አወረድን :: እርሱም የእነዚህ ሕዝቦች መጨረሻ ያነጉ ሲሆኑ ስራቸው መቆረጥ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَآءَ أَهْلُ ٱلْمَدِينَةِ يَسْتَبْشِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy67. የከተማይቱም ሰዎች የሚበሳሰሩ ሆነው መጡ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ ضَيْفِى فَلَا تَفْضَحُونِ
Amharic Translation - Africa Academy68. ሉጥም አለ፡- «እነዚህ እንግዶቼ ናቸውና አታጋልጡኝ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَلَا تُخْزُونِ
Amharic Translation - Africa Academy69. «አላህንም ፍሩ አታሳፍሩኝም።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوٓا۟ أَوَلَمْ نَنْهَكَ عَنِ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy70. «ከዓለማት ማንንም እንዳታስተናግድ አልከለከልንህምን?» አሉት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ هَٰٓؤُلَآءِ بَنَاتِىٓ إِن كُنتُمْ فَٰعِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy71. ሉጥም፡- «እነዚህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው። የምትፈጽሙ ከሆናችሁ አግቧቸው።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَعَمْرُكَ إِنَّهُمْ لَفِى سَكْرَتِهِمْ يَعْمَهُونَ
Amharic Translation - Africa Academy72. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዕድሜህ እንምላለን እነርሱ በእርግጥ በስካራቸው ውስጥ ይዋልላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَخَذَتْهُمُ ٱلصَّيْحَةُ مُشْرِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy73. ጩኸቲቱም ጸሐይ የወጣችባቸው ሲሆኑ ያዘቻቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَجَعَلْنَا عَٰلِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ
Amharic Translation - Africa Academy74. ላይዋንም ከታችዋ አደረግን:: በእነርሱም ላይ የሸክላ ድንጋዮችን አዘነብንባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّلْمُتَوَسِّمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy75. በዚህ ውስጥ ለተመልካቾች በእርግጥ ብዙ መገሰጫዎች አሉበት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّهَا لَبِسَبِيلٍ مُّقِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy76. እርሷም ከተማይቱ በቀጥታ መንገድ ላይ ናት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً لِّلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy77. በዚህ ውስጥ በእርግጥ ለአማኞች መገሰጫ አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن كَانَ أَصْحَٰبُ ٱلْأَيْكَةِ لَظَٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy78. እነሆ የአይካ ሰዎችም በእርግጥ በዳዮች ነበሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱنتَقَمْنَا مِنْهُمْ وَإِنَّهُمَا لَبِإِمَامٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy79. ከእነርሱም ተበቀልን ሁለቱም የሉጥና የአይከት ሕዝቦች ከተሞች በእርግጥ በግልጽ መንገድ ላይ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ كَذَّبَ أَصْحَٰبُ ٱلْحِجْرِ ٱلْمُرْسَلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy80. የሒጅር ሰዎች መልዕክተኞቹን በእርግጥ አስተባበሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَءَاتَيْنَٰهُمْ ءَايَٰتِنَا فَكَانُوا۟ عَنْهَا مُعْرِضِينَ
Amharic Translation - Africa Academy81. ተዓምራታችንን ሰጠናቸው ከርሷም ዘንጊዎች ነበሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَانُوا۟ يَنْحِتُونَ مِنَ ٱلْجِبَالِ بُيُوتًا ءَامِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy82. ከኮረብታዎችም ቤቶችን ጸጥተኞች ሆነው ይጠርቡ ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَخَذَتْهُمُ ٱلصَّيْحَةُ مُصْبِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy83. ያነጉ ሲሆኑ ጩኸት ያዘቻቸው (ወደሙ)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَآ أَغْنَىٰ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَكْسِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy84. ይሠሩት የነበሩትም ምንም አልጠቀማቸዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا خَلَقْنَا ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَآ إِلَّا بِٱلْحَقِّ وَإِنَّ ٱلسَّاعَةَ لَـَٔاتِيَةٌ فَٱصْفَحِ ٱلصَّفْحَ ٱلْجَمِيلَ
Amharic Translation - Africa Academy85. ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በእውነት እንጂ በላግጣ አልፈጠርንም:: ሰዓቲቱም በእርግጥ መጪ ናት:: መልካምን ይቅርታ አድርግላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ رَبَّكَ هُوَ ٱلْخَلَّٰقُ ٱلْعَلِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy86. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ እርሱ ያልነበረን ነገር ሁሉ ፈጣሪው፤ አዋቂው ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ ءَاتَيْنَٰكَ سَبْعًا مِّنَ ٱلْمَثَانِى وَٱلْقُرْءَانَ ٱلْعَظِيمَ
Amharic Translation - Africa Academy87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሚደጋገሙ የሆኑን ባለ ሰባት አንቀጽንና ታላቁንም ቁርኣን በሙሉ በእርግጥ ሰጠንህ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَا تَمُدَّنَّ عَيْنَيْكَ إِلَىٰ مَا مَتَّعْنَا بِهِۦٓ أَزْوَٰجًا مِّنْهُمْ وَلَا تَحْزَنْ عَلَيْهِمْ وَٱخْفِضْ جَنَاحَكَ لِلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy88. ከእነርሱ ከከሓዲያን ብዙዎችን ወገኖች በእርሱ ወደ አጣቀምንበት ጸጋ ዓይኖችህን አትዘርጋ፤ በእነርሱም ላይ ባያምኑ አትዘን፤ ክንፍህንም ለአማኞች አለዝብ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقُلْ إِنِّىٓ أَنَا ٱلنَّذِيرُ ٱلْمُبِينُ
Amharic Translation - Africa Academy89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ግልጽ አስፈራሪ እኔ ነኝ።» በል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَمَآ أَنزَلْنَا عَلَى ٱلْمُقْتَسِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy90. (ሰዎችን ለማገድ የመካን በሮች) በተከፋፈሉት ላይ እንደ አወረድነው (ቅጣት አስፈራሪያችሁ ነኝ በል)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ جَعَلُوا۟ ٱلْقُرْءَانَ عِضِينَ
Amharic Translation - Africa Academy91. እነርሱም እነዚያ ቁርኣንን ክፍልፍሎች ያደረጉ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَوَرَبِّكَ لَنَسْـَٔلَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy92. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጌታህ እንምላለን ሁላቸውንም እንጠይቃቸዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
عَمَّا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy93. ይሠሩት ከነበሩት ነገር ሁሉ
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱصْدَعْ بِمَا تُؤْمَرُ وَأَعْرِضْ عَنِ ٱلْمُشْرِكِينَ
Amharic Translation - Africa Academy94. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለጽ:: አጋሪዎችንም ተዋቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّا كَفَيْنَٰكَ ٱلْمُسْتَهْزِءِينَ
Amharic Translation - Africa Academy95. ተሳላቂዎችንም ሁሉ እኛ በቅተንሃል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ يَجْعَلُونَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy96. እነርሱም እነዚያ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን ያደረጉ ናቸው:: በእርግጥም ፍጻሜያቸውን ወደፊት ያውቃሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ نَعْلَمُ أَنَّكَ يَضِيقُ صَدْرُكَ بِمَا يَقُولُونَ
Amharic Translation - Africa Academy97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም በሚሉት ነገር ልብህ የሚጠብ መሆኑን እናውቃለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ وَكُن مِّنَ ٱلسَّٰجِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy98. ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው:: ከሰጋጆቹም ሁን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ ٱلْيَقِينُ
Amharic Translation - Africa Academy99. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውነቱም ነገር (ሞት) እስኪመጣልህ ድረስ ጌታህን ተገዛ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→